ሩሲያ በግዝፈቱ ሁለተኛ የሆነውን የዩክሬን የኃይል ጣቢያ ተቆጣጠረች
ዩክሬን ጦርነቱ ሲጀመር ከዓለም ትልቅ የሆነው የኒውክለር ኃይል ጣቢያ መቆጣጠር ችላ ነበር
ሩሲያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጦር ቀደም ብላ ወደ ተቆጣጠረቻቸው ወደ ሜሊቶፖል፣ዛፖሪዥያ እና ኬርሶን መላኳ ዩክሬን ገልጻለች
የሩሲያ በዩክሬን በግዝፈቲ ሁለተኛ የሆነውን የኃይል ጣቢያ ተቆጣጠረች፤ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ደቡባዊ ዩክሬን ልካለች።
ዩክሬን ጦርነቱ ሲጀመር ከዓለም ትልቅ የሆነው የኒውክለር ኃይል ጣቢያ መቆጣጠር ችላ ነበር
የሩሲያ ጦር የኃይል ጣቢያውን መቆጣጠሩንና በደቡባዊ ዩክሬን ወደሚገኙ ሶስት ግዛቶች ብዛት ያላቸው የሩሲያ ወታደሮች መላካቸውን የዩክሬን ፕሬዝደንት አማካሪ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሩሲያ ይህን ያደረገችው ዪክሬን በሩሲያ የተያዙ ቦታዎችን እንደምታስለቅቅ እየገለጸች ባለችበት ወቅት ነው።
በሶስት ሳምንታት ውስጥ ለሩሲያ ትልቅ ድል ነው በተባለው ጥቃት በሩሲያ የሚደገፉ ኃይሎች በሶቬት ጊዜ የተቋቋመውን እና በከሰል የሚሰራውን ቩህለሂሪስክ የኃይል ጣቢያን ተቆጣጥረዋል።
የዩክሬን ፕሬዝደንት አማካሪ የሆኑት ኦሌክሲይ አረስቶቪች በምስራቃዊ ዶምባስ ያለው የኃይል ጣቢያ በሩሲያ ኃይሎች መያዙን አረጋግጠዋል።
ሩሲያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጦር ወደ ሜሊቶፖል፣ዛፖሪዥያ እና ኬርሶን መላኳ ከማጥቃት ወደ መከላከል መሸጋጉሯን ያሳያል ብሏል ዘገባው። ዩክሬን ጦርነቱ እንደተጀመረ አካባቢ በሩሲያ የተያዘውን የኬርሶን ግዛት ለማስመለስ እንደምትንቀሳቀስ ግልጽ አድርጋለች።
በደቡብ የሚገኘው የሚገኘው የዩክሬን ጦር 66 የጠላት ወታደሮች መግደሉን አስታውቋል። ሩሲያ ማይኮላይቭ የምትባለውን የዩክሬን ከተማ በሮኬት ደብድባለች።
ሮይተርስ ሁለቱ ከካላት የሚያቀርቡትን ሪፖርት ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል።
ሩሲያ የኔቶ ጦር ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋት ለደህንነቷ እንደማያሰጋት በመግለጽ ነበር በዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ያወጀችው።
ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬንን ትጥቅ ማስፈታት እና የናዚን አስተሳሰብ ማጥፋት የዘመቻው አላማ መሆኑን ሩሲያ መግለጿ ይታወሳል።
በሩሲያ ርምጃ የተቆጡት ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉ ማእቀብ በሩሲያ ላይ ጥለዋል። የዶምባስ ግዛትን ነጻ የማውጣት የወሰነቸው ሩሲያ አሁንም በደቡብ እና ምሰራቃዊ ዩክሬን ጦርነት እያካሄደች ትገኛለች፡