ዩክሬንና ብሪታንያ በጋራ በመሆን የሩሲያ አብራሪዎችን ለማስኮብለል ያዘጋጁት ሚስጥራዊ እቅድ ተጋለጠ
የሩሲያ አብራሪዎች የጦር ጄታቸውን ለዩክሬን አስረክበው ከኮበለሉ ለእያንዳንዳቸው 2 ሚሊየን ዶላር ተዘጋጅቶ ነበር
ዩክሬን Su-24M፣ Su-34 እና Tu-22M3 የሚባሉ የሩሲያ የጦር ጄቶች ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ነበራት
ሩሲያ የብሪታንያ እና የዩክሬን አብራሪዎቿን ለማስኮብለል እና የሚያበሩትን ጄት ካስረከቡ በነፍስ ወከፍ 2 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ያዘጋጁትን ሚስጥራዊ እቅድ አጋለጠች።
የሩሲያ የፌደራል የደህንነት አገልግሎት በብሪታኒያ የሚደገፍ እና ለእያንዳንዳቸው የሩሲያ የጦር አውሮፕላን አብራሪዎች 2 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል እና በአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ የተዘጋጀ እቅድ ላይ መድረሱን አስታውቋል።
የዩክሬን እና የብሪታኒያ ሚስጥራዊ ኦፕሬሽንን ዝርዝር ሁኔታን የያዙ ማስረጃዎች በሩሲያ መገናኛ ብዙሃን የተለቀቁ ሲሆን፤ ማስረጃዎቹም የዩክሬን የደህንነት ኃላፊዎች ለሩሲያ አብራሪዎች የላኩት የስልክ ምልእክቶች እና የድምጽ ማስረጃዎችን የያዘ ነው።
በተገኘው የድምጽ ማስረጃ ላይ ማንነቱ ያልተለየ አንድ የዩክሬን የደህንነት ኃላፊ፤ “መጀመሪያ ላይ በአንድ ሚሊየን ዶላር ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ ነን፤ በመቀጠልም ሌላ አንድ ሚሊየን ዶላር እንደምንከፍላችሁ አረጋግጥላችዋለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል።
በተጋለጠው ሚኒስጥራዊ እቅድ መሰረትም የሩሲያ አብራሪዎች በዩክሬን የጦር አውሮፕላኖች የተጠለፉ በማስመሰል ዝቅ ብለው በመብረር የያዙትን የጦር ጄት በዩክሬን እጅ ወደ ሚገኝ የአውሮፕላን ማረፊያ አንዲያሳርፉ ለማድረግ ነበር።
ኪቭ Su-24M፣ Su-34 እና Tu-22M3 የሚባሉ የሩሲያ የጦር ጄቶች ላይ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት የደህንት ባለስልጣኑ ያስታወቁ ቢሆንም፤ ሆኖም ግን እቅዱ የሩሲያ አብራሪዎች ለሀገራቸው የፌደራል የደህንነት ተቋም በሰጡት ጥቆማ ሊደረስበት ችሏል።
ሮሲያ 24 የተባለው የሀገሪቱ ብሄራዊ ጣቢያ ባወጣው መረጃ ሞሶኮ ከሪስቶ ግሮሴቭ ተባለ የምርመራ ጋዜጠኛ የማስኮብለያ ቅድመ ክፍያዎችን ለአብራሪዎች የመክፈል ሂደት ውስጥ ከብሪታኒየ የስለላ ተቋም ጋር ሲሰራ ነበረ በሚል መክሰሷ ጠቅሷል።
ከሪስቶ ግሮሴቭ የተባለው የምርመራ ጋዜጠኛ ቤሊንካት ለተባለ ድረ ገጽ የሚሰራ ሲሆን፤ ድረ ገጹ ሩሲያ የተቃዋሚ መሪ አሌኪሲ ናላቭል መመረዟን ያጋለጠ ነበር።
የምርመራ ጋዜጠናው ከሪስቶ ግሮሴቭ ዩክሬን የሩሲያ የጦር አውሮፕላን አብራሪዎችን ለመስክብለል የያዘችው እቅድ አውነት እንደሆነ አረጋግጧል።
ለአብራሪዎች ከገንዘብ በተጨማሪም በፈረንሳይ እና በጀርመን ጭምር መኖሪያ እየተመቻቸላቸው አንደሆነም የምርመራ ጋዜጠናው አረጋግጧል።