የሩሲያ መርማሪዎች በሞስኮው ጥቃት የተከሰሱ ግለሰቦች ቤተሰቦች ላይ ምርመራ አካሄዱ
ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ የታጃክ ዝርያ ያላቸው አራት ግለሰቦች በሽብርተኝነት ተከሰዋል
የሩሲያ ባለስልጣናት እንደገለጹት ከሆነ ተጠርጥረው ከያዙት ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ ጥቃቱን በማድረስ መሳተፋቸውን አምነዋል
የሩሲያ መርማሪዎች በሞስኮው ጥቃት የተከሰሱ ግለሰቦች ቤተሰቦች ላይ ምርመራ አካሄዱ።
የሩሲያ መርማሪውች ወደ ታጂኪስታን በማቅናት ከሞስኮ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደ የሙዚቃ ድግስ ላይ ጥቃት በማድረስ የተከሰሱ አራት ተጠርጣሪ ቤተሰቦች ላይ ምርመራ አካሂደዋል።
ሮይተርስ ሶስት የታጂኪ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው የታጂክ የጸጥታ አካላት የተከሳሾቹን ቤተሰቦች ከቫክዳት፣ጊሳር እና ከሩዳኪ ከተሞች ወደ ዋና ከተማዋ ዱሻንቤ አምጥተዋቸዋል።
በታጂክ በኩል ያለውን ምርመራ ፕሬዝደንት ኢሞማሊ ራክሞን ራሳቸው አየመሩት መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል። ፕሬዝደንቱ በጉዳዩ ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት ይፋዊ አስተያየት "ይህ አሳፋሪ እና አስከፊ ክስተት ነው"፤ የታጂክ ወላጆች ልጆቻቸውን በመጥፎ ነገር ተጽዕኖ ከሚያሳድሩባቸው እንዲጠብቁ አሳስበዋል።
ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ የታጃክ ዝርያ ያላቸው አራት ግለሰቦች በሽብርተኝነት ተከሰዋል።በተጨማሪም ሌሎች ሶስት የታጃኪ ግለሰቦች በመተባበር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አይኤስ አይኤስ ጥቃቱ ሲፈጸም የሚያሳይ ቪዲዮ በማጋራት "ጥቃቱን ያደረስኩት እኔ ነኝ" ብሎ ኃላፊነት ወስዷል። ነገርግን ቡድኑ የጥቃት አድራሾቹን ማንነት ይፋ አላደረገም።
በዚህ ወር መጀመሪያ የታጃኪ ፕሬዝደንት ራክሞን አክራሪ ሙስሊሞች የታጃክ ወጣቶችን እየሰበኩ መሆናቸውን እና ይህም ለውጭ ታጣቂ ቡድኖች እና የስለላ ድርጅቶች ተጋላጭ እንዳያደርጋቸው ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።
10 ሚሊዮን ህዝብ ያላት የቀድሞ ሶቬት ህብረት አባል የነበረችው ታጂኪስታን የሞስኮ የቅርብ አጋር ነች፣ የሩሲያ የጦር ሰፈርም በሀገሪቱ ይገኛል።
የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በሩሲያ የሚሰሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ በሚልኩት ገንዘብ ላይ ጥገኛ የሆነ ነው።
የሩሲያ ባለስልጣናት እንደገለጹት ከሆነ ተጠርጥረው ከያዙት ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ ጥቃቱን በማድረስ መሳተፋቸውን አምነዋል።
ከ130 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት በማቀናበር አይኤስአይኤስ ኃላፊነት እንደሚወስድም፣ ሩሲያ ግን ይህ አልተዋጠላትም።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከዚህ ጥቃት ጀርባ ዩክሬን እንዳለችበት እና ጥቃት አድራሾቹን ለመቀበል በዩክሬን በኩል መንገድ ለመክፈት ዝግጅት ነበር ብለዋል።ዩክሬን ይህን ክስ ውድቅ አድርጋዋለች።