ለዩክሬን የድሮን ጥቃት በማድረስ የተጠረጠረ ሩሲያዊ ሞስኮ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከከፈተች ሁለት አመት ያስቆጠረ ሲሆን ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል
ኤፍኤስቢ እንዳስታወቀው በሀገር ክህደት ተጠርጥሮ የተያዘው ሩሲያዊ ግለሰብ ድሮን በመገጣጠሙን እና ለዩክሬን መተኮሱን አምኗል ብሏል
ለዩክሬን የድሮን ጥቃት በማድረስ የተጠረጠረ ሩሲያዊ ሞስኮ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የሩሲያ ፌደራል ሴኩሪቲ ሰርቪስ(ኤፍኤስቢ) በዛሬው እለት እንዳስታወቀው በሀገር ክህደት ተጠርጥሮ የተያዘው ሩሲያዊ ግለሰብ ድሮን በመገጣጠሙን እና ለዩክሬን መተኮሱን አምኗል ብሏል።
ኤፍኤስቢ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው በስም ያልጠቀሰው ይህ ግለሰብ "በሩሲያ መከላከያ ግቢ ውስጥ የሀሰት ኢላማ በመፍጠር ድሮን ገጣጥሞ ተኩሷል"።
ኤፍኤስቢ ግለሰቡ ዩክሬንን ለሚደግፈው 'ፍሪደም ኦፍ ሩሲያ ሌጅን' ለተባለው የዩክሬን ደጋፊ ለሆነው ታጣቂ ቡድን ይሰራ ነበር ማለቱን ሮይተርስ ኢንተርፋክስ ኒውስ ኤጀንሲን ጠቅሶ ዘግቧል።
ከቅርብ ወራት ወዲህ ኪቭ ሩሲያ ውስጥ የነዳጅ ማጣሪያ እና የብረት ፋብሪካዎችን ጨምሮ በኢኮኖሚ መሰረተ ልማቶች ላይ የምትሰነዝረውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከከፈተች ሁለት አመት ያስቆጠረ ሲሆን ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።
በቅርቡ የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን ባደረገው ጦርነት ወሳኝ የተባለችው አቭዲቪካን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን በመቆጣጠር ባለው ሰኔ ወር ባክሙትን ከተቆጣጠረ ወዲህ ከፍተኛ የሚባል ድል አስመዝግቧል።
ዩክሬን እነዚህን ከተሞች ለመልቀቅ የተገደደችው የምዕራባውያን ወታደራዊ ድጋፍ ቶሎ ባለመድረሱ እና ወታደሮቿ ከበባ ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ መሆኑን ገልጻለች።