የአለም ጤና ድርጅት በአዲሱ ክትባት ዙሪያ ከሩሲያ ጋር መወያየቱን አሰታወቀ
የአለም ጤና ድርጅት በአዲሱ ክትባት ዙሪያ ከሩሲያ ጋር መወያየቱን አሰታወቀ
የአለም ጤና ድርጅት ሩሲያ ባጸደቀችው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ውጤታማነት ዙሪያ ከሀገሪቱ ጋር መነጋገሩን ገልጿል።
ሩሲያ በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የሚሆን የኮሮና ክትባት ይፋ ስታደርግ ከአለም የመጀመሪያዋ ሀገር ለመሆን ችላለች። የሩሲያ ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ሁሉንም አሰፈላጊ የሆኑ ሂደቶችን ያለፈና ውጤታማነቱ የተረጋገጠ መድሃኒት ነው ብለዋል።
ፕሬዘዳንቱ የራሳቸው ልጅ ክትባቱን መውሰዷንና ከተከተበች በኋላ የሰውነት ሙቀቷ መስተካከሉንና ከፍተኛ የጸረ እንግዳ አካል ማግኘቷን ገልጸው ነበር።
የመድሃኒቱ ፈዋሽነት አለምአቀፍ ጥርጣሬ ጭሯል፤ምክንያቱ ደግሞ ለፍተሻ የወሰደው ከሁለት ወር በታች መሆኑና ለፍተሻ ጥቂት ሰዎች በመሳተፋቸው ነው ተብሏል።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ታሪክ ጃስርቪክ ስለመድሃኒቱ ውጤታማነትና አሰፈላጊውን ሂደት ሰለማለፉ ከሩሲያ ጋር እየተወያየን ነው ብለዋል።