አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ህግ አውጭ ም/ቤት አባል ጆ ባይደን በአሸባሪነት እንዲፈረጁ ጠየቁ
ፕሬዝድንቱ "ኖርድ ስትሪም" የተሰኘው የሩሲያ ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ጥቃት እንዲደርስበት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል
የሩሲያ ህግ አውጪ ምክር ቤት አባል ፕሬዝዳንት ባይደን "አሸባሪ" ናቸው ብለዋል
የሩሲያ ህግ አውጭ ም/ት አባል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በአሸባሪነት እንዲፈፈረጁ ጠየቁ።
ሩሲያ እና አሜሪካ በተለይም ከዩክሬን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ግንኙነታቸው ከሙቼውም ጊዜ በላይ መሻከሩ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ቤት በፍተሸ ተገኙ ስለተባሉ ሚስጥራዊ ሰነዶች ዋይት ሀውስ ምን አለ?
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን መላኳን ተከትሎ አሜሪካ ሌሎች ሀገራትን በማስተባበር የጦር መሳሪያ ለዩክሬን በመስጠት ላይም ትገኛለች።
ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያ ወደ ጀርመን እና ስካንዲቪዲያን ሀገራት ጋዝ የምትልክበት "ኖርድ ስትሪም" የተሰኘው መሰረተ ልማት ላይ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ጥቃት ደርሶበታል።
በዚህ መሰረተ ልማት ላይ የተጠና እና የተቀናጀ ጥቃት ደርሶበታል የተባለ ሲሆን ሩሲያ አሜሪካንን ጠርጥራት ነበር።
አሜሪካ ከሩሲያ የደረሰባትን ክስ በወቅቱ ውድቅ ያደረገች ቢሆንም ከሰሞኑ የወጣ የምርመራ ዘገባ መሰረት ጥቃቱ በዋሽንግተን መፈጸሙ ተገልጿል።
የአሜሪካው የምርመራ ጋዜጠኛ ሲሙር ሄርሽ በሰራው ዘገባ የኖቶ ጦር አባል የሆነው የአሜሪካ ባህር ሀይል ጥቃቱን እንዳደረሰው ዘግቧል።
ይህ የምርመራ ዘገባ መውጣቱን ተከትሎ የሩሲያ ህግ አውጪ ምክር ቤት አባል የሆኑት ቪያችስላቭ ቮሎዲን ፕሬዝዳንት ባይደንን " አሸባሪ" ሲሉ ጠርተዋል።
ቮሎዲር አክለውም አሜሪካ ወዳጆቿ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ሆላንድ ነዳጅ ያገኙባቸው የነበረውን የሀይል መሰረተ ልማት ላይ ጥቃት አድርሳለች ሲሉም ተናግረዋል።
አሜሪካ በበኩሏ በጋዜጠኛ ሴይሙር ሄርሽ የቀረበውን ዘገባ ሀሰት እና ድርሰት ነው ስትል ውድቅ አድርጋለች።