ፕሬዝዳንት ባይደን ቤት በፍተሸ ተገኙ ስለተባሉ ሚስጥራዊ ሰነዶች ዋይት ሀውስ ምን አለ?
በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መኖሪያ ቤት ባለፈው አርብ ፍተሸ መደረጉ ተነግሯል
በፍተሸው ስድስት አይነት ሚስጥራዊ ሰነዶች ተገኝተዋል ነው የተባለው
የአሜሪካው ነጩ ቤተ መንግስት (ዋይት ሀውስ) በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቤት የተገኙ ሚስጥራዊ ሰነዶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫው "በፕሬዝዳንት ባይደን መኖሪያ ቤት ባለፈው አርብ ፍተሻ የተደረገው የግል ጠበቃቸው በበጎ ፍቃድ ለፍትህ ክፍል ካሳወቁ በኋላ ነው" ብሏል።
የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ኢን ሳምስ በፍተሻ ስለተገኘው ሰነድ ይዘት ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ነገር ግን "ባይደን ስለ ፍተሻው ምን እየተካሄደ እንደነበር ያውቁ ነበር" ብለዋል።
ቃል አቀባዩ እንዳሉት በፕሬዝዳንት ባይደን ቤትና ቢሮ ውስጥ ስለተገኙት ሚስጥራዊ ሰነዶች የዋይት ሀውስ ጠበቃ በሪፐብሊካኖች ቁጥጥር ስር ላለው ምክር ቤት የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢ ደብዳቤ ልከዋል።
በፍተሻው ስድስት አይነት ሚስጥራዊ ሰነዶች ናቸው ተገኙ የተባሉት። ከምክር ቤት አባልነታቸው ጀምሮና በባራክ ኦባማ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት በነበሩ ጊዜ የነበሩ ሚስጥራዊ ሰነዶች በፍተሻው ከተገኙት መሀል ናቸው ተብሏል።
ጉዳዩ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገሪቱ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ከተኙ ሚስጥራዊ ሰነዶች ጋር ተያይዟል።
በዚህም የመሪዎች የሰነድ አያያዝ ጥያቄ ውስጥ የገባ ሲሆን፤ ማወዛገቡንም ቀጥሏል።
ዋይት ሀውስ "የባይደን ቡድን ሰነዶቹን አሳልፎ ሰጥቷል፤ ከባለስልጣናት ጋርም ተባብሯል" ሲል ጉዳዩ ለየቅል እንደሆነ ጠቁሟል።