ሩሲያ የአሜሪካውን ቻትጅፒቲ የሚገዳደር አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ሰራሁ አለች
ሲስተማ ጅፒቲ የተሰኘው ይህ የሩሲያ ቴክኖሎጂ ከስታንፎርድ ዩንቨርሲቲ ጋር በትብብር የጠሰራ ነው
ሲስተማ ጅፒቲ ጥናቶችን መጻፍ፣ ፕሮግራሚንግ እና ሌሎች ስራዎችን ያከናውናል ተብሏል
ሩሲያ የአሜሪካውን ቻትጅፒቲ የሚገዳደር አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ መስራቷን ገለጸች።
ከወራት በፊት የአሜሪካው ኦፕን አይ ኩባንያ ቻትጅፒቲ የተሰኘ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
ይህ አሜሪካ ሰራሽ አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ግጥም እና ዜማን ጨምሮ በርካታ ስራዎችን ይሰራል መባሉ በአንድ ሳምንት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን ማፍራት አስችሎት ነበር።
- ቻይና የአሜሪካውን ቻትጂፒትን ለመገዳደር "ኢርኒ ቦት" የተሰኘ ፈጠራ ይፋ አደረገች
- “ቻትጂፒቲ” በርካቶችን እያስደመመ ያለው አዲስ መተግበሪያ ምን የተለየ አደረገው…?
ይሁንና ቻይና እና ሌሎች ግዙፍ ኢኮኖሚ እና ህዝብ ያላቸው ሀገራት አሜሪካ ሰራሹን ቴክኖሎጂ ዜጎቻቸው እንዳይጠቀሙት እገዳ ጥለው ነበር።
ቻይና ባሳለፍነው ሳምንት በባይዱ የቴክኖሎጂ ኩባያ አማካኝነት አርኒ ጀፒቲ የተሰኘ አርቲፊሻል ቴክኖሎጂዋን ይፋ ያደረገች ሲሆን ሩሲያም የራሷን ስሪት ይፋ አድርጋለች።
በሩሲያ መዲና ሞስኮ መሰረቱን ያደረገው ኩባንያ ሲስተማ ጅፒቲ የጠሰኘ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስራውን ይፋ አድርጓል ተብሏል።
ይህ የቻት ቦት ቴክኖሎጂ ከስታንፎርድ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር መሰራቱን አርቲ ዘግቧል። ቴክኖሎጂው በተለይም መሰረታቸውን ሩሲያ ላደረጉ የቢዝነስ እና የመንግስት ተቋማት እበንደተሰራ ተገልጿል።
ሲስተማ ጅፒቲ ፈጣን የሖነ የጽሁፍ አገልግሎቶችን እና ሂደቶችን በመስጠት የተደነቀ ሲሆን ቱቶሮችን፣ ጥናታዊ ጽሁፎችን እና ሌሎች ውይይቶችን ማከናወን ያስችላልም ተብሏል።