አዲስ ይፋ የተደረገው ጥናት የስርዓተ-ፆታ የእድሜ ልዩነት በስተጀርባ ያለውን እውነታ አረጋግጧል
ሴቶች በዓለም ዙሪያ ከወንዶች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ይታወቃል።
በታሪክ ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ረጅም ዕድሜ እንደሚኖሩ የሚነገር ሲሆን፤ በሁለቱ ፆታዎች መካከል ያለው የእድሜ ልዩነት እየጨመረ መምጣቱን በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ጥናቶች አመላክተዋል።
ከሰሞኑ በአሜሪካ በካሊፎርኒያ ዩኒቭርሲቲ ተሰርቶ ይፋ በተደረገ ጥናትም ሴቶች ከወንዶች በበለጠ 6 ዓመታን የመኖር እድል እንዳላቸው የተመላከተ ሲሆን፤ ይህም ከሩብ ምዕተ ዓመት ወዲህ ትልቁ የእድሜ ልዩነት መሆኑ ተነግሯል።
ዓለም አቀፍ የተመራማሪዎች ቡድን ከዚህ ቀደም ባወጡት ጥናት ደግሞ የሴቶች የእድሜ ርዝመት ከወንዶች በአማካይ 8 በመቶ እንደሆነም አስታውቀዋል።
የወንዶች እድሜ ከሴቶች ለምን ያጥራል?
የወንዶች እድሜ ከሴቶች እድሜ ለማጠር የስነ ህይወት ጉዳይ ቀዳሚውን ስፍራ ቢይዝም፤ ባህላዊ ልማዶች ወንዶች ችግሮቻቸውን እንዲደብቁ ስለሚያደርግ ለጤና ችግር፣ በጭንቀት ለመኪሰት ራስን ማጥፋት ችግሮች ተጋላጭ ስለሚያደርጋቸው ነው ተብሏል።
በፈረንጆቹ በ2020 እና በ2021 ደግሞ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው የሞት ልዩነት እያደገ የመጣው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ሲሆን፤ ቫይረሱ ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ሞት ላይ ትልቅ ተፅእኖ እንደነበረውም ተነግሯል።
የወንዶች ቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን ከበሽታ መመከላከል ስርዓታቸው መዳከም ጋር ግንኙነት አለው የተባለ ሲሆን፤ ይህም ከልብ እና መተንፈሻ አካል ጋር ለተያያዘ ችግር በቀላሉ እንዲጋለጡ እና እንዲሞቱ እንደሚያደርግም ተነግሯል።
ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ ጤናማ የሆነ አመጋገብን መከተል የወንች እድሜ ከሴቶች እንዲያጥር ከሚያደርጉት ምክንያች ውስጥ ይገኛሉ።
ህመም ሚያጋጥማቸው ጊዜም ወንዶች ወደ ህክምና በመሄድ የህክምና ክትትል ማድረግ እና ሀኪም ማማከር ላይ ያላቸው ልምድ ከሴቶች ያነሰ መሆኑም ተነግሯል።
እንደሁም አኃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ወንዶች ህይወትን አደጋ ላይ በሚጥሉ እንደ በመኪና አደጋ ወይም በጠመንጃ ውጊያ የመሞት እድላቸው ከፍተኛ ነው።
ተመራማሪዎች የወንድና የሴት የእድሜ ልዩነት በእንስሳት ላይ አለ ያሉ ሲሆን፤ በተለያዩ አይንት አንስሳት ላይ በተደረገ ጥናትም ሴት እንስሳት ከወንድ እንስሳት እድሜያቸው በአማካይ በ18 በመቶ እንደሚረዝም አስታውቀዋል።
ለምሳሌ የሴቶች አንበሳ የእድሜ ርዝመት ከወንዶች በአማካይ በ50 በመቶ እንደሚረዝምም አስታውቀዋል።