ኒጀር ከፈረንሳይ ጋር ያላትን ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧ ይታወቃል
የሩሲያ ጦር አሰልጣኖች የኒጀር ብሄራዊ ጦርን ለማሰልጠን ኒሜይ መግታቸው ተገለጸ።
የሩሲያ ጦር አሰልጣኖች የኒጀር መግባታቸው ሞስኮ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በሚገኘው የምዕራብ አፍሪካ የሳህል ቀጠና ተጽእኖዋን እያሳደገች ስለመምጣቷ ያመላክታል።
ባሳለፍነው ረቡእ ወታደራዊ ስልጠና ለመስጠት የኒጀር ዋና ከተማ ኒሜይ የገቡት የሩሲያ ጦር ስፔሻሊስቶች የተለያዩ ጦር መሳሪያዎችን ከእቃ ጫኝ አውሮፕላን ሲያወርዱም ታይተዋል ነው የተባለው።
የሩሲያ ወታደረዊ አሰልጣኞች የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ይዘው ኒጀር መግባታቸውንም የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባወጣው ዘገባ አመላክቷል።
ከሩሲያ ጦር አሰልጣኞች መካከል አንዱ ከኒጄር ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረገው ቆይታ፤ “እዚህ የተገኘነው የኒጄር ብሄራዊ ጦርን ለማሰልጠን እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር ለማሳደግ ነው” ብሏል።
አሰልጣኞቹ ኒጀር ኒሜይ የገቡት በሩሲያ እና በኒጀር ጁንታ መካከል በሰላምና ፀጥታ ዘርፍ በጋራ ለማስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ነው።
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኒጀር ጁንታ ባለፈው ዓመት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ ከሞስኮ ጋር ያለውን ግንኙነት እያጠናከ መጥቷል።
ኒጀር ከፈረንሳይ ጋር የነበራትንና ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረውን ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧ ይታወቃል።