የዩክሬን ምርኮኞችን አሳፍሮ የነበረው የሩሲያ አውሮፕላን መከስከሱ ተነገረ
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር እንደገለጸው አውሮፕላኑ በሩሲያ የጦር ምርኮኞች ሊቀየሩ የነበሩ 65 የዩክሬን የጦር ምርኮኖች አሳፍሮ ነበር
ሩሲያ፣ አውሮፕላኑን ሆነ ብላ ተኩሳ መትታለች ስትል ዩክሬንን ከሳለች
የዩክሬን ምርኮኞችን አሳፍሮ የነበረው የሩሲያ አውሮፕላን መከስከሱ ተነገረ።
የዩክሬን ምርኮኞችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው ኢዩሽን ll-76 የተሰኘው የወታደራዊ ትራስፖርት አውሮፕላን በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ መከስከሱን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር እንደገለጸው አውሮፕላኑ በሩሲያ የጦር ምርኮኞች ሊቀየሩ የነበሩ 65 የዩክሬን የጦር ምርኮኖች አሳፍሮ ነበር።
የሩሲያው ሪያ ዜና አገልግሎት መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበው አውሮፕላኑ 6 የበረራ ባለሙያዎችን፣ ስድስት ጠባቂዎችን ጨምሮ 74 ሰዎችን ይዞ ሲበር ነው አደጋው ያጋጠመው።
በሩሲያ ፖርላማ ህግ አውጭ እና የቀድሞ ጀነራል የሆኑት አንድሬ ካርታፖሎቭ በፖርላማ ስብሰባ ወቅት አውሮፕላኑ በሶስት ሚሳይል ተመቶ መከስከሱን ተናግረዋል።
ሩሲያ እና ዩክሬን የጦር ምርኮኛ ልውውጥ ብዙ ጊዜ አድርገዋል።
ሮይተርስ በጉዳዩ ላይ ከዩክሬን በኩል በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ለመግኘት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ገልጿል።
ለሩሲያ ደህንነት ቅርብ የሆነው የባዛ ቴሌግራም ቻናል የተለቀቀው ቪዲዮ በቤልጎሮድ ግዛት በምትገኘው ያብሎኖቮ መንደር አውሮፕላኑ ወደ መሬት ሲወድቅ እና ከፍተኛ እሳት ሲቀጣጠል ያሳያል።
የአካባቢው አስተዳዳሪው ቪያቸስላቭ ግላድኮቭ ከቤልጎሮድ ከተማ በሰሜንምስራቅ በኩል ያልታወቀ ክስተት መፈጠሩን እና ምርመራ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
አስተዳዳሪው መርማሪዎች እና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታው ላይ ደርሰዋል ብለዋል።
Il-76 እቃ፣ ወታራዊ እቃዎች እና መሳሪያ ለማጓጓዝ የሚያገለግል ወታደራዊ አውሮፕላን ነው።
ሩሲያ፣ አውሮፕላኑን ሆነ ብላ ተኩሳ መትታለች ስትል ዩክሬንን ከሳለች።