ህይወት ለማዳን ህይወታቸውን ያጡት የሩስያው ሚኒሰትር
ሚንስትሩ የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን በቁፋሮ ስራ ላይ ሳሉ ህይወታቸው አልፏል ተብሏል
የሚኒሰትሩ ህልፈት በአሰቃቂ ሁኔታ መሆኑ ጉዳዩን አሳዛኝ አድርጎታልም ነው የተባለው
የሩሲያ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሚኒስትር የሰውን ህይወት ለማዳን ሲሞክሩ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡
የሩስያው የአስቿኳይ ጊዜ ሁኔታ ሚኒስትር ህይወታቸው ያለፈው በኖርልስክ አርክቲክ ከተማ አቅራቢያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚደረግበት ጊዜ “ ሕይወት የማዳን ”ኃላፊነታቸው ሲወጡ ነው ተብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ ኢቭጂኒ ዚኒቺቭ ህይወትን ለማዳን በቁፋሮ ስራ ላይ ሳሉ ለሞት የሚዳርግ አደጋ እንዳጋለጠቸውንም ነው የተገለጸው። መስርያ ቤታቸውም ዚኒቺቭ “ የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን ሲሞክሩ ህይወታቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ ሊያልፍ ችለዋል” ብለዋል፡፡
በጉብኝታቸው በኖርልስክ ከተማ አዲስ የእሳት አደጋ ጣቢያ ሲመረምሩም ነበር ሚነሲትሩ።
የአር.ቲ. ዋና አዘጋጇ ማርጋሪታ ሲሞንያን በአደጋው ጊዜ “ሚኒሰትሩ እና የካሜራ ባለሙያ ጠርዝ ላይ ቆመው ነበር ከዛም የካሜራ ባለሙያው ተንሸራቶ ወደ ውሃው ውስጥ ወደቀ። በርካታ ሰዎች በስፍራው የነበሩ ቢሆንም ፣ ዚንክቼቭ ወደ ውሃው እስኪወድቁና ኩፉኛ አስኪመቱ ድረስ ምን እየሆነ እንዳለ ለመገንዘብ አልቻሉም ነበር”
“እሱ እንደ አዳኝ ሞተ - በሰላም እረፍ”ም ስትል ኃሳቧን ገልጻለች ማርጋሪታ ሲሞንያን፡፡ማርጋሪታ የካሜራ ባለሙያው ህይወት ማለፉንም ጭምር አስታውቃለች፡፡