“ኦክሲጅን መጣጩ” ከአየር ላይ ኦክሲጅን አጥፍቶ ጠላትን የሚገድለው አደገኛው የሩሲያ የጦር መሳሪያ
በT-72 ታንክ ላይ የሚገጠመው መሳሪያው በ90 ሰከንድ ውስጥ ኢላማውን ይመታል
መሳሪያው በአየር ላይ ጥቁር ደመናን በማሰራጨትና ከሳንባ ውስጥ ኦክሲጅን በመምጠጥ ጠላትን በማፈን ይገድላል
ዩክሬን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ መጀመሯን ተከትሎ ሩሲያ ከሰሞኑ አዲስ የጦር መሳሪያ ብቅ ማደረጓ ተነግሯል።
"TOS 1" የተባለውና ኦክሲጅን መጣጩ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ አደገኛ የጦር መሳሪያ፤ ኦክሲጅንን ከአየር ላይ በመምጠጥ ጠላትን የሚገድል ነው ተብሏል።
የሩሲያ የጦር መሳሪያ አምራች ቮስቶክ ቡድን መሪ ኦሌግ ቼክሆቭ እንደተናገሩት፤ "TOS 1" የጦር መሳሪያን ሶልስቲበክ ላውንቸር የተባለው የሩሲያ ጦር ቡድን ኖቮዶንስኪ በተባለ ስፍራ የዩክሬን ጦር ጥቃትን ለመቀልበስ ጥቅም ላይ አውሏል ብለዋል።
የሩሲያ ጦር አባላት መሳሪያውን በመጠቀም ሁለት ብረት ለበስ የዩክሬን ጦር ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም በርካታ የዩክሬን ሰራዊትን ገድሏለ ያሉ ሲሆን፤ መሳሪያው ባለበት ግንባር የሩሲያ ጦር የለቀቀበው ቦታ የለም ሲሉም ተናረዋል።
“ኦክሲጅን መጣጩ” "TOS 1" ምን የተለየ ያደርገዋል?
በT-72 ታንክ ላይ የሚገጠመው መሳሪያው በ90 ሰከንድ ውስጥ ኢላማውን ይመታል የተባለ ሲሆን፤ የጠላት የአየር መከላከያ ትጥቆችን እና ብረት ለበስ መሳሪያዎችን እንዲሁም በጣም የተደበቁ የምሽግ ቦታዎችን ሊያጠፋ ይችላል።
ከ24-30 የሚደርሱ የ220 ሚሊሜትር ካሊበር ሮኬቶችን ተሸክሞ በ6 ሰከንድ ውስጥ በመተኮስ በአቅራቢያው ያሉ ኢላማዎችን ማለትም ከ400 ሜትር እስከ 6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያሉትን ኢላማዎች ያጠፋል።
"TOS 1" የተባለውና ኦክሲጅን መጣጩ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ አደገኛ የጦር መሳሪያ፤ ጥቁር ደመና ጋዝን አየር ላይ በመበተን በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የምንተነፍሰው አየር እንዳይኖር ያደርጋል የተባለ ሲሆን፤ ኦክሲጅንን ከሰዎች ሳምባ ውስጥ በመምጠጥ ጠላት በመታፈን እንዲሞት ያደርጋል።
ከዚህ በተጨማሪም መሳሪያ በሚፈጥረው ፍንዳዋ ወቅት የሚፈጥረው ግጭት የአጥንት መሰበርን፣ የአይን መፍሰስን፣ የጆሮ ታምቡር መበጠስን እንዲሁም ወደ ውስጥ ደም የመፍሰስ ችግርን እንደሚያስከትልም ተመላክቷል።