የ14 አመት እስር የተፈረደባቸው ሩሲያዊ የሃይፐርሶኒክ ሚሳይል ሳይንቲስት ማን ናቸው?
የ77 አመቱ ማስሎቭ ክሳቸው በዝግ ችሎት ሲታይ ከቆየ በኋላ በሴንትፒተርስብግ ከተማ የሚገኝ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል
በሩሲያ የሃይፐርሶኒክ ሚሳይል ማበልጸግ ወሳኝ ሚና የነበራቸው የፊዚክስ ባለሙያ በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሰው የ14 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል ተብሏል
በሩሲያ የሃይፐርሶኒክ ሚሳይል ማበልጸግ ወሳኝ ሚና የነበራቸው ሩሲያዊው የፊዚክስ ባለሙያ አናቶሊ ማስሎቭ በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሰው የ14 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል ተብሏል።
የ77 አመቱ ማስሎቭ ክሳቸው በዝግ ችሎት ሲታይ ከቆየ በኋላ በሴንትፒተርስብግ ከተማ የሚገኝ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ እንደተላለፈባቸው ሮይተረስ ዘግቧል።
ማስሎቭ ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ ፍርዱን ተቃውመዋል። ማስሎቭ ከሳይቤሪያን ኢንስቲትዩት ከመጡት እና በሀገር ክህደት ተከሰው ከ2022 ጀምሮ በእስር ላይ ከሚገኙነት የሃይፐርሶኒክ ሚሳይል ሳይንቲስቶች ውስጥ አንዱ ናቸው።
ሌሎቹ ሁለቱ ማለትም አሌክሳንደር ሽፕሊዩክ እና ቫለሪ ዝቨግስቴቭ ክሳቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ክሳቸውን እየተከታተሉ ያሉት እና ማስሎቭ ከሌሎች ሳይንቲስቶች ጋር በሆን የአየር መከላከያ ስርአትን ከድምጽ በ10 እጥፍ ፈጥኖ የሚመታ ዘመናዊ የሃይፐርስኒክ መሳሪያ ለማበልጸግ የቲዎሪ ስራ እያከናወኑ ነበር።
ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ በጦር መሳሪያ ዘርፍ የአለም መሪ እንደሆነች ይናገራሉ።
እንደማስሎቭ ሁሉ ሽፕልዩክ እና ዝቨግስቴቭም ጥፋኛ አለመሆናቸውን እና በአለምአቀፍ ስብሰባ ያቀረቧቸው ጹህፎች ጥብቅ መረጃዎችን ያካተቱ አይደሉም ሲሉ ተከራክረዋል። እነሱ እንደሚሉት ይህ ክስ በሩሲያ ምርምር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው ብለዋል።
ክሪሚሊን በወቅቱ በሰጠው ምላሽ ግለሰቦቹ "ከፍተኛ ክስ እንደቀረበባቸው" ገልጾ ጉዳዩም የደህንነት ጉዳይ ነው ብሎ ነበር።
የሩሲያው ሚዲያዎች የማስሎቭን ጠበቃ ጠቅሰው እንደዘገቡት ሳይንቲስቱ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት የመጨረሻ ንግግር ሙሉ ህይወታቸውን በምርምር ማሳለፋቸውን እና ሀገራቸውን እንደሚክዱ አስበው እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ማስሎቭ በዚህ አመት መጀመሪያ የልብ ህመም እንዳጋጠማቸው የገለጸው ጠበቃው የተላለፈው የረጅም ጊዜ እስር ከሞት ፍርድ ጋር የሚስተካከል ነው ብሏል።