ሩሲያ ለዩክሬን የተለገሱ የምእራባውያን ታንኮችን ያወደሙ ወታደሮችን ሸለመች
የአሜሪካው አብርሃም እና የጀርመኑ ሊዮፓርድ ዘመናዊ ታንኮች ለዩክሬን በብዛት የተሰጡ ናቸው
ሩሲያ የአሜሪካና ጀርመን ሰራሽ ታንኮችን ላወደሙ ወታደሮች ማበረታቻ እንደምትሰጥ ከዚህ በፊት ቃል ገብታ ነበር
ሩሲያ ከምዕራባዊያን ለዩክሬን የተሰጡ ታንኮችን ያወደሙ ወታደሮችን ሸለመች።
በአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት አስተባባሪነት ዩክሬን ከሩሲያ እየደረሰባት ያለውን ጦርነት እንድትመክት እና በድል እንድትቋጭ በርካታ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ወደ ኪየቭ ተጓጉዘዋል።
የአሜሪካው አብርሃም እና የጀርመኑ ሊዮፓርድ ዘመናዊ ታንኮች ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን የምድር ላይ ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ ወሳኝ ሚናይ ጫወታሉ ተብሏል።
ሩሲያ በበኩሏ ለዩክሬን የሚሰጠው የጦር መሳሪያ ጦርነቱን ከማራዘም ውጪ ሚና አይኖረውም በሚል ምላሽ የሰጠች ሲሆን ከምዕራባዊያን ለዩክሬን የሚሰጡ መሳሪያዎችን አወድማቸዋለሁ ብላም ነበር።
የሩሲያ ወታደሮችም አሜሪካ ሰራሽ የሖኑ አብርሃም እና የጀርመኑ ሊዮፓርድ ታንኮችን ካወድሙ አልያም ከማረኩ እሸልማለሁ ስትል ገልጻም ነበር።
በዚህ መሰረትም ሩሲያ የጀርመን እና አሜሪካ ሰራሽ የሆኑ ዘመናዊ ታንኮችን ላወደሙ ወታደሮቿ ሽልማት መስጠቷን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስት ሰርጊ ሼጉ እንዳሉት የጀርመኑን ሊዮፓርድ እና የአሜሪካ የጦር መሳሪያዎችን ላወደሙ የሩሲያ ወታደሮች የገንዘብ እና የወርቅ ጀግና ሜዳሊያ መሸለማቸውን ተናግረዋል።
እስካሁንም 10 ሺህ ወታደሮች ከ16 ሺህ በላይ የዩክሬን እና ለዩክሬን የተረዱ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች መውደማቸው ተግጿል።
አንድ የጠላት የጦር ተሽከርካሪ ላወደመ 596 ዶላር አንድ ታንክ ላወደመ ደግሞ አንድ ሺህ ዶላር እየጠሸለመ ነው የተባለ ሲሆን አንድ የጦር አውሮፕላን ላወደመ ደግሞ ከ3 ሺህ ዶላር በላይ መሸለሟን ሚኒስትሩ አክለዋል።