ፖለቲካ
ሩዋንዳ ከቀድሞ ቅኝ ገዥዋ ቤልጂየም ጋር ያላትን ግንኙነት አቋረጠች
ቤልጂየምን በሩዋንዳ ላይ ያልተገባ አስተያየት በመስጠት የከሰሰችው ኪጋሊ የቤልጅየም ዲፕሎማቶች ሀገሪቱን በ48 ሰአታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ አዛለች

ቤልጀምም በሩዋንዳ ዲፕሎማቶች ተመሳሳይ እርምጃ ወስዳለች
አፍሪካዊቷ ሩዋንዳ በዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ረፐብሊክ(ዲአርሲ) ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ ከቀድሞ ቅኝ ገዥዋ ቤልጂየም ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ በመሉ አቋርጣለች።
ቤልጂየምን በሩዋንዳ ላይ ያልተገባ አስተያየት በመስጠት የከሰሰችው ኪጋሊ የቤልጅየም ዲፕሎማቶች ሀገሪቱን በ48 ሰአታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ አዛለች።
ቤልጀምም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዳለች።
የቤልጅየም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክዚም ፕሪቮት ሩዋንዳ የወሰደችው እርምጃ "ተመጣጣኝ አለመሆኑንና በማንስማማበት ወቅት ሩዋንዳ ንግግር ለማድረግ ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳይ ነው"ብለዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም የሩዋንዳ ዲፕሎማቶች በሀገሪቱ ተቀባይነት የላቸውም ብለዋል።
ሩዋንዳ በምስራቅ ኮንግ ጥቃት እየፈጸመ ያለውን የኤም23 አማጺ ቡድን በመደገፍ ክስ እየቀረበባት ሲሆን የአፍሪካ ሀገራት ተኩስ እንዲቆም ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።
አማጺ ቡድኑ በመንግስት ኃይሎች ላይ ጥቃት በመክፈት በምስራቅ ኮንጎ ያሉ ሁለት ትላልቅ ከተሞችን ተቆጣጠሯል።