ርዋንዳ ሁለት ሳተላይቶችን ከዓለም ቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት ልትገዛ ነው
ርዋንዳ ከ2 ዓመት በፊት ርዋሳት-1 የተባለችን አንድ አነስተኛ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ማስወንጨፏ ይታወሳል
ሳተላይቶቹ ሲናሞን-217 እና ሲናሞን-937 ይሰኛሉ ተብሏል
ርዋንዳ ከዓለም ቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት (ITU) ሁለት ሳተላይቶችን ለመግዛት ጠየቀች፡፡
ጥያቄው በርዋንዳ ህዋ ኤጀንሲ ነው ሲናሞን-217 እና ሲናሞን-937 የተባሉ ሳታላይቶችን ለመግዛት የቀረበው፡፡
በህብረቱ የተቀመጡ የግዢ መስፈርቶችን በማሟላት ጥያቄውን ከቀናት በፊት ማቅረቡንም ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡
ጥያቄው ህብረቱ ካሉትና ከሚያስተዳድራቸው 327,320 ሳታላይቶች መካከል ሲናሞን-217 እና ሲናሞን-937 የተባሉትን ለመግዛት የቀረበ ነው፡፡
የርዋንዳ ህዋ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍራንሲስ ንጋቦ ጥያቄው ርዋንዳን የአፍሪካ ህዋ ኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ በማሰብ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡
ETRSS-1 የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ የጠፈር በር-ETRSS-1
ጥያቄው የሳተላይት ፍሪኩዌንሲንና በመሬት ምህዋር ላይ የተመዘገበ ቦታን (orbital slots) ለመያዝ እና ወደፊት ሳተላይት ማምጠቅ መቻላችንን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ መንግስት የህዋ ኢንዱስትሪ ዘርፍን የሃገራዊ ልማቱ አካል ለማድረግ ከያዘው ውጥን ጋር ተጣጥሞ የሚሄድ ነው እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው ገለጻ፡፡
ኢትዮጵያ የሳተላይት መገጣጠሚያ ማዕከልን ልትገነባ ነው
ከአሁን ቀደም የሳተላይት መረጃዎችን ከተለያዩ ሃገራት እና ተቋማት ታገኝ የነበረችው ርዋንዳ ከ2 ዓመት በፊት ርዋሳት-1 (RWASAT-1) የተባለችን አንድ አነስተኛ የመሬት ምልከታ ሳተላይት አስወንጭለች፡፡
RWASAT-1 ሶስት ርዋንዳውያን እና በቶኪዮ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች የተሰራች ናት፡፡
ETRSS-1የተሰኘች አነስተኛ የመሬት ምልከታ ሳተላይትን ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ማለዳ ወደ ህዋ ያመጠቀችው ኢትዮጵያ 6 ዩኒት ኪዩብ የምድር ምልከታ ሳተላይትን ባለፈው ዓመት ማስወንጨፏ እና በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ግዙፍ የብዝሓ-ሳተላይት መረጃ መቀበያ ጣቢያን መገንባቷ ይታወሳል፡፡