በቅርቡ ከኢራን የጠለፋ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን ጠላፊ ግለሰቦች ከያዘች በኋላ መሆኑን አሜሪካ አስታውቃለች
በቅርቡ ከኢራን የጠለፋ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን ጠላፊ ግለሰቦች ከያዘች በኋላ መሆኑን አሜሪካ አስታውቃለች
የአሜሪካ ፍትህ ዲፓርትመንት ባለፈው ሀሙስ እንዳስታወቀው ሶስቱ ኢራናውያን ከኤሮስፔስና ከሳተላይት ተቋም መረጃ ሰርቀዋል በሚል የጠረጠረቻቸውን ነው ክስ የመሰረተችባቸው፡፡
ይህ የአሜሪካ እርምጃ በቅርቡ ከኢራን የጠለፋ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን ጠላፊ ግለሰቦች ከያዘች በኋላ መሆኑን የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ ረዳት አቃቤ ህግ ጀነራል ጆን ደምርስ እንደገለጹት በጠለፋ የተጠረጠሩ ኢራናውያን ሲያዙ ይህ በሳምንት ውስጥ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፤የውጭ ሀገራት የአሜሪካን ፍሬ ለመስረቅ ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡
የአሜሪካ መንግስት እነዚህ ሶስት ግለሰቦች ባልደረቦቻቸውንና ትምህርትን በመጠቀም መጥለፊያ የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ማውረዳቸውን አቃቤ ህግ ገልጿል፡፡
ከሳሽ ኣቤ ህግ እንደገለጸው ሶስቱ ተከሳሾች ለኢራኑ ሪቮሉሽናሪ አብዮት ጠባቂ ሲሆን አሜሪካ ይህን ድርጅት እንደ አሸባሪ ነው የትቆጥረው፡፡ ሮይተርስ በአሜሪካ ከሚገኘው የኢራን ሚሽን መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት አልተሳካም ብሏል፡፡