ለባለቤቷ ገዳይ ይቅርታ በማድረግ ልጆቻቸው እንዲጋቡ የፈቀደችው ሩዋንዳዊት እናት
በርናደት “ዶናታ ሁለ ነገሯ ስለወደድኩት ነው የልጄ ሚስት እንድትሆን ያልተቃወምኩት’’ ብላለች
በርናደት “ልጆቻችን ምንም ኃጢያት የለባቸውም፤ ልጆቹ ተፋቅሯል እናም ማንም ሊያስቆማቸው አይገባም” ብላለች
ሩዋንዳዊቷ እናት በርናደት ሙካካቤራ በ1994ቱ የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ላይ ባለቤቷን የገደለባትን ግለሰብ ይቅር ከማለት አልፋ ለዘላቂ ፍቅር ስትል ወንድ ልጇን የአባቱ ገዳይ ሴት ልጅን እንዲያገባ መፍቀዷ ተስመቷል።
በሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ የተፈጠሩ ቁስሎችን የተቀያየሙ ማህበረሰቦች ለማስታረቅ የሀገሪቱ ካቶሊካዊ ቤተ- ክርስትያን በምታደርገው ጥረት ውስጥ የበኩሏን ሚና ስትጫወት የቆየችው ሙካካቤራ “ህመምህን ለማዳን ከፈለክ ማፍቀር አለብህ” ብላለች።
እናት ማካካቤራ “ልጆቻችን ከተፈጸመው ድርጊት ጋር ምንም የሚያገናኛቸው ነገር የለም፤ ልጆቹ ተፋቅረዋል እናም ማንም ሊያስቆማቸው አይገባም” ብላለች።
የበርናደት ባለቤት ገዳይ ግራቲየን ኒያሚናኒ የተባለ ከሁቱ ጎሳ የሚወለድ ሩዋናዳዊ ሲሆን፤ ከጭፍጨፋው በኋላ ቱትሲዎች ስልጣን ሲይዙ፤ እንደማንኛውም የወንጀሉ ተሳታፊ ፍርድ ቤት ቀርቦ ብይን የተሰጠው ነው።
ይሁን እንጂ በተለያዩ ጊዜያት ይካሄዱ በነበሩ የፍርድ ቤት ውሎዎች ከሳሾች አሉን የሚሏቸው ማስረጃዎች አቅርበው ተከሻሾችን ይሞግቱ ስለነበር፤ በ2004 ግራቲየን የበርናደትን ባለቤት ካቤራን እንዴት እንደገለው ዝርዝር ሁኔታዎች በማስረዳት ይቅርታ ጠይቋት ነበር። በርናደትም ብትሆን ወዲያውኑ ይቅርታውን ተቀብላዋልች።
በዚህም ገዳዩ የተፈረደበትን የ19 ዓመታት የእስር ፍርድ 10 ዓመታት ከታሰረ በኋላ የተቀሩትን የእስር ዓመታት የሁለት ዓመታት ማህበረሰባዊ አገልግሎት በነጻ በመስጠት እንዲያካክስ ተደርጓል።
የበርናደት ባለቤት ሲገደል ገና የ9 ዓመት ታዳጊ የነበችው የገዳዩ ግራቲየን ያንኩሪጀ ሴት ልጅ ዶናታ ወደ በርናደት ቤት በመሄድ አንዳንድ የቤት ጓዳ ስራዎች በማገዝ እንዲሁም ግዲያው ሲፈጸም ገና የ14 ዓመት ታዳጊ ከነበረው የበርናደት ወንድ ልጅ አልፍረድ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር ጀመረች።
“አባቴ ባሏ ስለገደለላትና ሌላ የሚያግዛት ሰው አጠገቧ ስላልነበር የአልፍረድ እናትን እየሄድኩ ሳግዛት ነበር” የምትለው ልጅ ዶናታ ፤”አልፍረድ ሊያፈቅረኝ የቻለው እናቱን በማግዝበት ወቅት በነበሩ ሁኔታዎች ይመስለኛል” ብላለች።
በልጅቷ ውሳኔ ውስጧ የተነካው በርናደት በበኩሏ ‘”አባቷ ባለቤቴን ስለገደለውና ልጄ በአዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ይማር ስለነበር ያለሁበት ሁኔታ ገብቷት ነው እኔን ያገዘችኝ፤ እኔም ሁለ ነገሯ ስለወደድኩት ነው የልጄ ሚስት እንድትሆን ያልተቃወምኩት” ብላለች።
ነገሩ በበርናደት በኩል ተቀባይነት ቢያገኝም ለግራትየን ግን ቀላል አልነበረም፤ የጋብቻ ጥያቄ ሲቀርብለት ተጠራጥሮ ነበር።
ዶናታ የነበረውን ሁኔታ ስታስታውስ “ብዙ ያስቀየምቁት ቤተሰብ እንዴትና ለምን ልጄን ፈለገ የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ያቀርብልኝ ነበር” በኋላ ግን ሁሉም ነገር ተቀብሎ ልጁን መርቆ ሰጥቷል ትላለች።
የሁለታችን ወላጆች ፈቃድ ካገኘን በኋላም እንደፈረንጆቹ በ2008 በአንድ የካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ጋብቻችን ልንፈጽም ችለናል ስትልም ዶናታ ትናገራለች።
ከ28 ዓመታት በፊት ሚያዝያ 71994 ከቀኑ 6፡00 የጀመረውና ለ100 ቀናት ያክል በሩዋንዳ ምድር የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አንድ ሚልዮን ገደማ ሰዎች የተገደሉበት እንደነበር ይታወሳል።