ካቡጋ በፈረንጆቹ በ1994 የተካሄደውን ዘርማጥፋት በገንዘብ በመደገፍ ሲፈለግ ቆይቶ ባለፈው ግንቦት ወር ነበር በፈረንሳይ የተያዘው
ካቡጋ በፈረንጆቹ በ1994 የተካሄደውን ዘርማጥፋት በገንዘብ በመደገፍ ሲፈለግ ቆይቶ ባለፈው ግንቦት ወር ነበር በፈረንሳይ የተያዘው
በፈረንጆቹ በ1994 የተካሄደውን የዘርማጥፋት በገንዘብ በመደገፍ የተጠረጠሩት ሩዋንዳዊ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሲፈለቁ ቆይተው በፈንሳይ ከተያዘ በኋላ በዘሄግ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፍርድቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ሊቀርብ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
በሩዋንዳ ከ800ሺ በላይ ቱሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች የተገደሉበትን ጭፍጨፋ በመደገፍ የተጠረጠሩት ፍሊሰን ካቡጋ በአለም በጣም ከሚፈለጉት ሰዎች መካከል መሆን ችለው ነበር፡፡
ከሩዋንዳ ባለሀብቶች መካከል አንዱ የሆኑት ካቡጋ የኢንተርሃሙየ የሚሊሻ ቡድን እንዲፈጠርና እንዲሁም ግጭት የቀሰቀሰውን ሊብሬ ደስሚሌ ኮሊንስ የተባለውን ሬድዩ በመርዳትም ተጠርጥረዋል፡፡ በዘር ማጥፋት ለተንቀሳቀሱት የሚውል ጎራዴ በፈረንጆቹ 1993 በመግዛት ተጠርጥረዋል፡፡
ባለስልጣናት ባለፈው ግንቦት ወር በፓሪስ የተያዘው ካቡጋ አሁን በተዘጋው አለምአቀፍ የሩዋንዳ የወንጀል ችሎት ላይ ተከሶ ነበር፤ ባለፈው ወር ከፈረንሳይ ወደ ዘሄግ መዛወሩ ይታወሳል፡፡
ጉዳዩን የያዙት ዳኛ ካቡጋ በአካል ወይንም በቪዲዮ መከታተል እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ከሳሾቹ ስለ ዝግጁነታቸው ለዳኛው እንደሚናገሩ ይጠበቃል፡፡