በሩዋንዳ በዘር ማጥፋት የተጠረጠረው ግለሰብ ለህክምና ወደ ዘ ሔግ ሊዛወር ነው
ካቡጋ የሩዋዳው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከተፈጸመ ከ25 ዓመታት በኋላ ባለፈው ግንቦት ወር በፓሪስ ተያዘ
በታንዛኒያ አሩሻ ጉዳዩን የያዙት ዳኛ የዝውውር ትዕዛዙን ማጽደቃቸውን አስታውቀዋል
በታንዛኒያ አሩሻ ጉዳዩን የያዙት ዳኛ የዝውውር ትዕዛዙን ማጽደቃቸውን አስታውቀዋል
በዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ በተፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች የተከሰሱት እና በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ ለሕክምና ምርመራ ወደ ዘ ሔግ ሊዛወር ነው መሆኑ ተገለጸ፡፡
ትዕዛዙ የመጣው የካቡጋ ጠበቆች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለረጅም ጊዜ የሚደረግ የአውሮፕላን በረራ ጉዞ በ 85 ዓመቱ ነጋዴ ላይ የጤና ችግር ያስከትላል በማለት በታንዛኒያ ከሚገኘው አሩሻ ይልቅ ወደ ሆላንድ ከተማ እንዲዛወር ከጠየቁ በኋላ ነው ፡፡
በታንዛኒያ አሩሻ ጉዳዩን የያዙት ዳኛ የዝውውር ትዕዛዙን ማጽደቃቸው ገልጸው የዓለም አቀፍ የወንጀል ልዩ ፍርድ ቤት የካቡጋን የእስር ሁኔታ እንዲያሻሽልም ማዘዛቸውን ሲጅቲኤን ዘግቧል፡፡
ዳኛው እንደገለጹት ይህ ሁኔታ በልዩ ሁኔታዎችን ውስጥ እንደሆነ አንስተው ተጠርጣሪው ካቡጋ ለጊዜው ወደ ሔግ ቅርንጫፍ ለዝርዝር የህክምና ምርመራ እንዲዛወሩ መታዘዙ ለፍትህ ሲባል የተደረገ ነው ብለዋል፡የተባበሩት መንግስታት ልዩ ፍርድ ቤት በሄግ እና በታንዛኒያ ቅርንጫፎች አሉት፡፡
ካቡጋ የሩዋዳው ዘር ማጥፋት ወንጀል ከተከናወነ ከ25 ዓመታት በኋላ ነው በፓሪስ አቅራቢያ ግንቦት ወር ላይ የተያዘው፡፡
ካቡጋ የሁቱተታቂ ቡድን የሆነውን ኢንተርሃምዌይንና ለዘር ጭፍጨፋው ግንባ ቀደም ተጠያቂ የሆነውን ሬዲዮ ቴሌቪዥን ሊብሬ ዴዝ ሚሌ ኮሊነስ ለማቋቋም እገዛ አድርጓል በሚል ነው የተከሰሰው፡፡ በፈረንጆቹ 1994 በተቀሰቀሰው የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከ800 ሺ በላይ ዜጎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡