ማሌማ በበኩላቸው በሀገሬ ነጭ ሊዳኘኝ አይችልም ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል
ታዋቂው የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት አባል ለአንድ ወር ታገዱ፡፡
የደቡብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ነጻነት ፓርቲ አባል የሆኑ ስድስት የምክር ቤት አባላት ለአንድ ወር ከስራ እና ከደመወዝ መታገዳቸው ተገልጿል፡፡
ከታገዱት አባላት መካከል ታዋቂው ጁሊየስ ማሌማ አንዱ ሲሆን ለእገዳው ምክንያት የሆኑት ደግሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ በምክር ቤቱ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ በመረበሻቸው ነው ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ባሳለፍነው የካቲት ወር ላይ በምክር ቤት ተገኝተው ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት የኢኮኖሚ ነጻነት ፓርቲ የተሰኘው ፓርቱ አባላት ተቃውሞ አሰምተው ነበር፡፡
የምክር ቤት አባላቱ ድርጊት ህገወጥ ነው በሚል የምክር ቤቱ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ላለፉት ወራት ምርመራ ሲካሄድ ቆይቶ አሁን ላይ አዲስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በዚህ ውሳኔ መሰረትም ጁሊየስ ማሌማን ጨምሮ ስድስት አባላት ለአንድ ወር ከደመወዝ እና ከስራ እንዲታገዱ ውሳኔ እንዳሳለፈ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማቋረጥ ወሰነ
ቅጣት በተላለፈባቸው የምክር ቤት አባላት ላይ ቅጣቱ ተፈጻሚ የሚሆነው ጥፋቱን ፈጽመዋል በተባለበት የካቲት ወር ላይ ይሆናልም ተብሏል፡፡
ጁሊየስ ማሌማ በበኩላቸው የዲሲፕሊን ውሳኔውን እንደማይቀበሉት የገለጹ ሲሆን ቅሬታ ለማቅረብም ወደ ነጩ ሰው ሄጄ አላመለክትም ሲሉ መናገራቸው ተገልጿል፡፡