ደቡብ አፍሪካ የእስር ማዘዣ ለወጣባቸው ፑቲን ያለመከሰስ መብት ሰጠች
ደቡብ አፍሪካ ለብሪክ ጉባኤ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍ/ቤት የእስር ማዘዣ ያወጣባቸው ባለስልጣናት እንደማይታሰሩ ተናግራለች
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የብሪክስ ጉባኤ ለፑቲን የመጀመሪያቸው ትልቅ የውጭ ጉዞ ይሆናል
የደቡብ አፍሪካ መንግስት ለብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ እና የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊ ለሚሆኑት ቭላድሚር ፑቲን እና ለሚመለከታቸው ባለስልጣናት "ዲፕሎማሲያዊ ያለመከሰስ መብት" ሰጥቷል።
ሀገሪቱ በሁለት ስብሰባዎች ላይ ለሚሳተፉ ተሳታፊዎች የዲፕሎማሲያዊ ያለመከሰስ መብት እንደሚሰጡ ተናግራለች።
የሀገሪቱ መንግስት መደበኛ ነው ባለው እንቅስቃሴ፤ በነሀሴ ወር ለሚካሄደው ጉባኤ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል።
የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚንስትር እርምጃው "መደበኛ" እና እንደዚህ አይነት አካሄዶች በደቡብ አፍሪካ ተመሳሳይ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ሲደረጉ እንደሚወጡ ገልጸዋል።
ያለመከሰስ መብቱ ከሰኔ አንድ እስከ ሁለት በኬፕታውን የሚሰበሰቡትን የውጭ ጉዳይ ሚነሰስትሮችንም ያጠቃልላል ሲል መንግስታዊ ጋዜጣ ሰኞ እለት ዘግቧል።
በሄግ የሚገኘው አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባለፈው መጋቢት ወር በዩክሬን የጦር ወንጀል ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።
ደቡብ አፍሪካ የፍርድ ቤቱ መስራች አባል በመሆኗ ፑቲንን በሀገሪቱ ውስጥ እያለ ማሰር አለባት።
ከሳምንታት በፊት የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሰረት ፑቲ ለስብሰባው ከመጡ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ጠቁመዋል።
የደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ እና ብራዚል መሪዎች የሚሳተፉበት የብሪክስ ጉባኤ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለፑቲን የመጀመሪያቸው ትልቅ የውጭ ጉዞ ይሆናል።