ከአንድ ወር በፊት የተፈጠረው የጸጥታ ሁከት እና ኮሮና ቫይረስ ለካቢኔዎቹ መታገድ ምክንያት ናቸው
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ የካቢኔዎች ሹም ሽር ማድረጋው ተሰምቷል።
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ እስርን ተከትሎ በአገሪቱ በተከሰተ ሁከት የ354 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ በርካቶች ንብረታቸውን ተዘርፏል፤ የአገሪቱ መሰረተ ልማቶች መውደማቸው ይታወሳል።
ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ በወቅቱ የአገሪቱ የደህንነት ተቋማት ይሄ ሀኩት እና ዚረፋ እንደሚከሰት መረጃ እንዳልነበራቸው ገልጸው ተቋማቱ ዝግጁነት እንደሚጎላቸውም ተናግረው ነበር።
በዚህም ምክንያት ፕሬዚዳንቱ የደህንነት ፤ኢኮኖሚ እና ጤና ሚኒስትሮች ላይ የካቢኔ ሹም ሽር ማካሄዳቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዚግቧል።
በዚህም መሰረት የመከላከያ፤ጤና እና የፋይናንስ ሚኒሰትሮቹን ከስልጣን በማንሳት አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል።
የአገሪቱን የስለላ ተቋም ተግሞ ከዚህ በፊት ከነበረበት ወደ ራሳቸው ጽህፈት ቤት አማምጣታቸው ተገልጿል።
ፕሬዚዳንቱ ይሄንን ያደረጉት የአገሪቱን ዜጎች ደህንነት መጠበቅ የመንግስታቸው ሃላፊነት በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል።
በደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እና ተጠቂዎች ቁጥር ማሻቀቡ ለጤና ሚኒስትሩ ከስልጣን ለመነሳታቸው ምክንያት እንደሆነም ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፖሳ በፈረንጆቹ 2018 ዓመት የቀድሞው አቻቸው ጃኮብ ዙማ በሙስና ምክንያት ከህዝብ በተነሳባቸው ተቃውሞ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ነበር ወደ መንበረ ስልጣኑ የመጡት።