ደቡብ ሱዳናውያን ከጤና ሚኒስቴር የሚወጣን መመሪያ ካልተገበሩ ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል-ፕሬዘዳንት ኪር
ደቡብ ሱዳናውያን ከጤና ሚኒስቴር የሚወጣን መመሪያ ካልተገበሩ ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል-ፕሬዘዳንት ኪር
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዛዳንት ሳልቫ ኪር “በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ በኋላ ከሀገር ወጡ”የሚለውን የሚዲያ ሪፖርቶች አጣጥለዋል፡፡
ፕሬዘደንት ኪር “እየተዋጋነው ያለው በሽታ መስሊም ወይንም ክርስቲየን ብሎ አይለይም፤ ዲንቃ ወይንም አቾሊ…ብሎም አይለይም፡፡ ይህ በቤት ውስጥ ያለ ምህረት የለሽ ጭራቅ ነው“ ብለዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ ስራቸውን አለመቀየራቸውን ገልጸዋል፡፡ ህዝቡ እንዲህ እይነት ፕሮፓጋዳ ውስጥ መግባት የለበትም ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት የደቡብ ሱዳንን ምክትል ፕሬዘዳንት ሪያክ ማቻርን ጨምሮ ዘጠኝ ከፍተኛ ባለስልጣናት በኮሮና መያዛቸው ተዘግቦ ነበር፡፡ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ራሳቸውን አግልለዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ ይሄን ያሉት በሀገሪቱ ስለ ኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ መረጃ እየሰጡ ባለበት ወቅት ነው፡፡ ፕሬዘዳንቱ በንግግራቸው ወቅት አንደገጹት በሀገሪቱ አሁን ላይ 600 በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች አሉ፡፡
ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ደቡብ ሱዳናውያን በጤና ሚኒስቴር የሚወጡ መመሪያዎችን ተግባር ላይ እንዲያውሉ ጥሪ አቅርበዋል፤ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ከሆኑ የሀገሪቱ የጤና ስርአት መሽከም እንደማይችል አስጠንቅተዋል፡፡
“አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ካልቻልን፣ቁጥሮች በፍጥነት ይጨምራሉ፤ በዚህም ችግር ውስጥ ያለ አገር እንሆናለን” ብለዋል ፕሬዘዳንት ኪር፡፡