ሳኖፊ ኬቭዛራ ከተሰኘው መድሃኒት የኮሮና ክትባትን ለማዘጋጀት ሲያደርግ የነበረውን ሙከራ አቋረጠ
በጽኑ የቫይረሱ ታማሚዎች ላይ የተደረገው ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳቶችን አስከትሏልም ተብሏል
ሙከራው የተቋረጠው ጥረቱ የሚፈለገውን ውጤት ባለማስገኘቱ ነው
ሳኖፊ ኬቭዛራ ከተሰኘው መድሃኒት የኮሮና ክትባትን ለማዘጋጀት ሲያደርግ የነበረውን ሙከራ አቋረጠ
ፈረንሳዊው መድሃኒት አምራች ኩባንያ ሳኖፊ ኬቭዛራ ከተሰኘው የሩማቶይድ አርትራይተስ (የመገጣጠሚያ ችግር) መድሃኒት የኮሮና ክትባትን ለማዘጋጀት ሲያደርግ የነበረውን ሙከራ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡
ሳኖፊ ሙከራውን ያቋረጠው መድሃኒቱ የቫይረሱን ታማሚዎች ከመፈወስ ይልቅ ተጓዳኝ የጤና እክሎችን በመፍጠሩ ነው፡፡
በመሆኑም ከአሁን በኋላ ሪጀነሮን ከተባለ ተቋም ጋር በመቀናጀት ያመረተውን መድሃኒት (ኬቭዛራ) ለኮሮና ክትባቶች ግብዓትነት ለመጠቀም የሚያደርገውን ክሊኒካዊ ሙከራ ማቋረጡን አስታውቋል ፡፡
መድሃኒቱ ህመሙ እምብዛም ያልጸናባቸውን ታማሚዎች እንኳን እጅግም ሊረዳ እንዳልቻለ ከአሁን ቀደም በተደረጉ ሙከራዎች መረጋገጡንም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡
ሳኖፊም ጉዳዩን በማስመልት ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፡፡
እንዳስታወቀው ከሆነም በጽኑ የቫይረሱ ታማሚዎች ላይ የተደረገው የሶስተኛ ደረጃ ክሊኒካል ሙከራ ሂደት የተፈለገውን ውጤት አላስገኘም፡፡
“ሙከራው ተስፋ ያደረግንበትን ውጤት ባያስገኝም ቡድናችን ሲያደርግ በነበረው ጥረት ኮርተናል”ያሉት የተቋሙ የዓለም አቀፍ ምርምር እና ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጆን ሪድ “አሁንም ክትባት ማዘጋጀትን ጨምሮ ወረርሽኙን ለማዋጋት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ቁርጠኛ ነን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡