ንጋኒ በተሰጠው ልዩ የመኖሪያ ፈቃድ መሰረት በሳውዲ መኖር እና ሀብት ማፍራት ይችላል
ሳውዲ አረቢያ ለቦክሰኛ ፍራንሲስ ንጋኑ ልዩ የመኖሪያ ፈቃድ ሰጠች፡፡
በትናንትናው ዕለት ከአንቶኒ ጆሽዋ ጋር የተፋለመው ካሜሪናዊው የቦክስ ስፖርተኛ ፍራንሲስ ንጋኑ ከሳውዲ አረቢያ ልዩ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝቷል፡፡
ንጋኑ ባገኘው የሳውዲ አረቢያ ልዩ የመኖሪያ ፈቃድ አማካኝነት በሀገሪቱ መኖር፣ መስራት እና የቢዝነስ ድርጅቶችን የማቋቋም መብት እንዳለው አል አረቢያ ዘግቧል፡፡
በዚህ ፈቃድ መሰረትም ንጋኑ ከመካ እና መዲና ውጪ ባሉ የሳውዲ አረቢያ ከተሞች መኖር እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ሳውዲ አረቢያ ለፍራንሲስ ንጋኑ ልዩ የመኖሪያ ፈቃድ የሰጠችው በሪያድ የተካሄዱ ሁለት ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መካፈሉን ተከትሎ ነው፡፡
በትናንትናው ዕለት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በትውልደ ናይጀሪያዊው እና በዜግነት ብሪታንያ የሆነው አንቶኒ ጆሽዋ ከካሜሩኑ ፍራንሲስ ንጋኑ መካከል መካሄዱ ይታወሳል፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሳውዲ አረቢያ ይባረር ይሆን?
ዓለም በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው ይህ የከባድ ሚዛን ቦክስ ውድድር የ34 ዓመቱ አንቶኒ ጆሽዋ በዝረራ ማሸነፍ ችሏል፡፡
70 ሚሊዮን ዶላር ለቅድመ ውድድር ወጪ የተደረገበት ይህ ውድድር ሁለቱም ተፋላሚዎች ከዚህ በፊት ስኬታማ መሆናቸውን ተከትሎ ውድድሩ ከዝረራ ይልቅ እስከ መጨረሻው ይቀጥላል ተብሎም ተጠብቆ ነበር፡፡
ፍራንሲስ ንጋኑ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይ በሪያድ ከሌላኛው የዓለም ከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ከሆነው ታይሰን ፉሪ ጋር ተወዳድሮ በዳኞች ውሳኔ መሸነፉ አይዘነጋም፡፡