ግለሰቦቹ በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሰው ጥፋተኛ መባላቸው ተገልጿል
ሳውዲ አረቢያ ሰባት ሰዎችን በሞት ቀጣች፡፡
የዓለማችን ነዳጅ ሀብታሟ ሀገር ሳውዲ አረቢያ ሰባት ሰዎችን በሞት ቀጥታለች፡፡
ሳውዲ አረቢያ በሽብር እና ሀገር መክዳት ወንጀል ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ናቸው የተባሉት እነዚህ ግለሰቦች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡
እንደ አልአረቢያ ዘገባ ከሆነ ጥፋተኛ የተባሉት እነዚህ ዜጎች የሳውዲ አረቢያን ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ጥለው እንደተገኙ ተገልጿል፡፡
ሳውዲ አረቢያ በአሜሪካ የተቋቋመው የቀይ ባህር ዘብ ጥምረትን እንደማትቀላቀል ተገለጸ
ግለሰቦቹ የሽብር ቡድኖችን እና ድርጅቶችን በገንዘብ ሲረዱ ተገኝተዋል የተባለ ሲሆን በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው የሞት ፍርድ ተላልፎባቸዋልም ተብሏል፡፡
የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው እነዚህ ሰባት ሰዎች የፍርድ ሂደታቸው በሀገሪቱ ልዩ ፍርድ ቤት ሲካሄድ እንደቆየም ተገልጿል፡፡
ይሁንና የሞት ፍርድ ስለተላለፈባቸው ግለሰቦች ማንነት፣ ፍርዱ መቼ እንደተላለፈ እና እንደተፈጸመ በዘገባው ላይ አልተጠቀሰም፡፡
ሳውዲ አረቢያ ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ ተጠርጣሪዎች ላይ የሞት ፍርድ ማስተላለፍ የሚያስችል ህግ ያላት ሲሆን የሞት ፍርድ የተላለፈባቸውን ሰዎች አንገታቸውን በሰይፍ በመቅላት ትፈጽማለች፡፡