በሳኡዲ አረቢያ ታሪካዊ የተባለ የፋሽን ትርኢት ተዘጋጀ
አብዛኞቹ ሞዴሎች ትከሻቸውን እና ደረታቸውን የሚያሳዩ ልብሶችን ለብሰው ታይተዋል
በሳኡዲ አረቢያ በመዋኛ ቦታ በተካሄደ የፋሽን ትርኢት በሞሮዃዊቷ ዲዛይነር ያስሚና ቃንዛል የተሰሩ የመዋኛ ልብሶች ቀርበዋል
በሳኡዲ አረቢያ ታሪካዊ የተባለ የፋሽን ትርኢት ተዘጋጀ።
በሳኡዲ አረቢያ በመዋኛ ቦታ በተካሄደ የፋሽን ትርኢት በሞሮዃዊቷ ዲዛይነር ያስሚና ቃንዛል የተሰሩ የመዋኛ ልብሶች ቀርበዋል።
አብዛኞቹ ሞዴሎች ትከሻቸውን እና ደረታቸውን የሚያሳዩ ልብሶችን ለብሰው ታይተዋል። "እውነት ነው ሀገሪቱ ወግ አጥባቂ ነች፤ ነገርግን የአረቡን አለም የሚወክል የሚያምር የመዋኛ ልብስ አዘጋጅተናል" ስትል ቁንዛል የኤኤፍፒ ተናግራለች።
"ወደ እዚህ ስንመጣ የመዋኛ ልብስ ፋሽን በሳኡዲ አረቢያ ታሪካዊ እንደሚሆን ተረድተናል፤ ምክንያቱም እንዲህ አይነት ፕሮግራም ሲዘጋጅ የመጀመሪያ ጊዜ ነው" ያለችው ቁንዛል በመሳተፏም ክብር እንደሚሰማት ጨምራ ገልጻለች።
ይህ የፋሽን ትርኢት የ"ሬድ ሲ ፋሸን ዊክ" በተጀመረ በሁለተኛው ቀን በሳኡዲ ምዕራብ ጠረፍ በሚገኘው ኤስቲ ሬዲስ ሬድ ሲ ሪዞርት ነው የተካሄደው።
ሪዞርቱ አልጋወራሽ ሞሀመድ ቢን ሳልማን በ2030 ለማጠናቀቅ ካቀዷቸው ጊጋ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ነው። በፈረንጆቹ 2017፣ ንጉስ መሀመድ ሳኡዲ አረቢያ በሌላው አለም የምትታወቅበትን ወግአጥባቂነት ለመቀየረ በተነሳሽነት ሰርተዋል።
ዱላ ይዘው የገበያ አዳራሽ ውስጥ እየገቡ ወንዶች እንዲጸልዩ የሚያሳድዱ ፖሊስችን ማገድን፣ ሲኒማን እንደገና ማስጀመርን እና ቅይጥ ፆታ እየየሚሳተፉበት የሙዚቃ ድግስ እንዲዘጋጅ መፍቀድን ጨምሮ በርካታ ለውጦችን አድርገዋል።
ባለፈው አርብ እለት በተካሄደው በዚህ የፋሽን ዲዛይን ትርኢት ላይ የተሳተፈው የሶሪያው የፋሽን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሳኡዲ አረቢያ ለአለም በሯን ክፍት ለማድረግ እና የፋሽን እና የቱራዝም ዘርፎችን ለማሳደግ እየሞከረች ስለሆነ የትርኢቱ መዘጋጀት እንዳላስገረመው ገልጿል።
ባለፈው አመት የታተመው የሳኡዲ ፋሽን ኮሚሽን መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በ2022 የፋሽን ኢንዱስትሪው ለሀገሪቱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ እድገት 1.4 በመቶ ድርሻ ያበረከተ ሲሆን 230ሺ ሰዎችን ቀጥሯል።