የሳኡዲ አረቢያ ኩባንያዎች በሩሲያ የኢነርጅ ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት ማድረጋቸውን አስታወቁ
የሳኡዲ አረቢያ ኩባንያዎች ኢንቨስት ያደረገችባቸው የሩሲያ የኢነርጅ ድርቶች ጋዝፕሮም፣ሮዝኔፍት እና በሉክኦይል ናቸው
ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ከጀመረች በኋላ በርካታ ምእራባውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ ማእቀብ መጣላቸው ይታወሳል
የሳኡዲ አረቢያ ኩባንያዎች በፈረንጆቹ ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 22፣ 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ በሩሲያ የኢነርጅ ድርጅቶች ላይ መዋእለ ነዋይ (ኢንቨስት) ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
የሳኡዲ አረቢያ ኩባንያዎች ኢንቨስት ያደረጉባቸው የሩሲያ የኢነርጅ ድርጅቶች ጋዝፕሮም፣ሮዝኔፍት እና በሉክኦይል ላይ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ በፈረንጆቹ የካቲት 24፣ 2014 በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ከጀመረች በኋላ አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ምእራባውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ ማእቀብ መጣላቸው ይታወሳል፡፡
የሳኡዲ ኩባንያዎች ለሶስት አመት የ3 ነጥብ4 ቢሊዮን ዶላር የሚቆይ ኢንቨስትመንት መፈጸሙን ኩባያው አስታውቋል፡፡ ኩባንያው እንዳስታወቀው 1ነጥብ 37 ቢሊዮን ሪያልስ በጋዝፕሮም፣196 ሚሊዮን ሪያልስ በሮዝኔፍት እና 410 ሚሊዮን ሪያልስ በሉክኦይል ኢንቨስት አድርጓል፡፡
ኢንቨስት ያደረገው የሳኡዲ ኩባንያ በዋናነት ባለቤትነቱ የሳኡዲ ልኡል አልጋ ወራሽ አልዋለድ ቢንታላል ሲሆን የሳኡዲ ሶቨሪን ዌልዝ ፈንድ እና ፐብሊከ ኢንቨስትመንት ፈንድ 18 ነጥብ 8 በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡
ሳኡዲ አረቢያ እና ሩሲያ በፈረንጆቹ 2017 የተቋቋመውን የፔትሮሊየም አቅራቢያ እና አጋር አማራቾችን ጥምረት ይመራሉ፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት ከከፈተች በኋላ ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ማእቀብ ጥለዋል፤እየጣሉም ይገኛሉ፡፡ ሩሲያ በበኩላ ምእራባውያን ሀገራት ምእራባውያን ሀገራት ነዳጃን በሩሲያ ገንዘብ ሩብል እንዲገዙ እስከማስገድድ ድርሳለች፡፡