ሳኡዲ አረቢያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት 40 ቢሊዮን ዶላር መመደቧን ገለጸች
ሀገሪቱ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማቱ ከአሜሪካ ሶት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ፈጽማለች
ስምምነቱ ከሰኔ ጀምሮ ይተገበራል ተብሏል
ሳኡዲ አረቢያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት 40 ቢሊዮን ዶላር መመደቧን ገለጸች፡፡
ይዓለማችን የነዳጅ ሀብታም ሀገር የሆነችው ሳውዲ አረቢያ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማት 40 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ማቋቋሟን አስታውቃለች፡፡
እንደ አልአረቢያ ዘገባ የሳውዲ አረቢያ ፐብሊክ ኢንቨስትመንት ከአሜሪካኖቹ ሀሮዊትዝ እና ሌሎች ኩባንያዎች ጋር የአጋርነት ስምምነት ፈጽሟል፡፡
ስምምነቱን ተከትሎ የሃሮዊትዝ ኩባንያ በሪያድ ቢሮውን እንደሚከፍት የተገለጸ ሲሆን ኩባንያው ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማት እና ትግበራ ግብዓት የሚሆኑ ሶፍትዌር እና ሌሎች ምርቶች ያቀርባል ተብሏል፡፡
ሳውዲ አረቢያ ለቦክሰኛ ፍራንሲስ ንጋኑ ልዩ የመኖሪያ ፈቃድ ሰጠች
በስምምነቱ መሰረትም ከቀጣዩ ሰኔ ወር ጀምሮ ስምምነቱ መተግበር ይጀምራል የተባለ ሲሆን ተጨማሪ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም ሊሳተፉ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ን የአሜሪካ ኩባንያዎች ለዓለም ቀድመው ያስተዋወቁ ሲሆን በመላው ዓለም ካሉ ተቋማት እና ሀገራት ጋር አብረን እንስራ ጥያቄ እየጎረፈላቸው ይገኛል ተብሏል፡፡
ቴክኖሎጂ ላይ የበለጠ መስራት ከሚፈልጉ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሳውዲ አረቢያ ከአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ስምምነቶችን እየፈተመች ትገኛለች፡፡
በመሀማድ ቢን ሳልማን የሚመራው የሳኡዲ አረቢያ ንጉሳዊ መንግስትም የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በሪያድ ቢሯቸውን በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡