ሳዑዲ ኔታንያሁ ፍልስጤማውያንን በማፈናቀል ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት ውድቅ አደረገች
ኔታያሁ “በሳዑዲ ግዛቷ ላይ የፍልስጤም መንግስት መመስረት ትችላች” ሲሉ መናራቸው ይታወሳል
ሳዑዲ "ይህ የወራሪና አክራሪ አስተሳሰብ የፍልስጤም ግዛት ለፍሊስጤማውያን ምን ማለት እንደሆነ አይረዳም" ብላለች
ሳውዲ አረቢያ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፍልስጤማውያንን በማፈናቀል ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት ውድቅ አደረገች።
የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው ማፈናቀልን አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ማድረጉን አስታቋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ከቀናት በፊት “ሳዑዲ አረቢያ ግዛቷ ላይ የፍልስጤም መንግስት መመስረት ትችላች” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታያሁ ቻናል 14 ከተባለ ሚዲያ ጋር በነበራቸው “የፍሊስጤም ግዛት” ለማለት በስህተት “የሳዑዲ ግዛት” ካሉ በኋላ ስህተታቸውን ሲያርሙ ተሰምተዋል።
የሳዑዲ መግለጫ የኔታንያሁ ስም ቢጠቅስም በቀጥታ በሳውዲ ግዛት የፍልስጤም መንግስት መመስረትን አስመልክቶ የተሰጡትን አስተያየት ግን አላነሳም ተብሏል።
ግብፅ እና ዮርዳኖስም “ሳዑዲ አረቢያ ግዛቷ ላይ የፍልስጤም መንግስት መመስረት ትችላች” የሚለው የእስራኤልን ሀሳብ ያወገዙ ሲሆን፣ ግብጽ ሀሳቡን “የሳውዲ ሉዓላዊነት ጥሰት” አድርጋ እንደምትወስድ አስታውቃለች።
የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው፤ ወንድም ሀገራት ያላቸው ግብጽ እና ዮርዳስ የኔታንያሁን ንግግር ውድቅ በማድረግ የሰጡትን አስተያየት እንደሚያክብር አስታውቋል።
"ይህ የወራሪና አክራሪ አስተሳሰብ የፍልስጤም ግዛት ለፍሊስጤማውያን ምን ማለት እንደሆነ አይረዳም" ሲል መግለጫው አመላክቷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ዋይትሃውስ እንደገቡ የጋዛ ፍርስራሽ እስኪጸዳ ድረስ ፍልስጤማውያን እንደ ግብጽ እና ዮርዳኖስ ባሉ ሀገራት እንዲጠለሉ ሃሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ዶናልድ ትራምፕ ጋዛን ለመቆጣጠር የያዙትን እቅድ በርካታ የዓለም ሀገራት በመቃወም ላይ ይገኛሉ።
የጋዛ ተፈናቃዮችን በቋሚነት እና በጊዜያዊነት እንዲያስጠልሉ ከትራምፕ ትእዛዝ የተሰጣቸው ግብጽ እና ዮርዳኖስ እቅዱን ውድቅ ያደረጉት ሲሆን፥ የፍልስጤም እና የአረብ መሪዎችም አጥብቀው ተቃውመውታል።
በትራምፕ ውሳኔ የተገረሙ እና የተደናገጡ የጋዛ ነዋሪ ፍሊጤየማውያንም “ጋዛን ለቀን አንወጣም” ሲሉ ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል።
“ነፍሳችንን ቢያስከፍለን እንኳን ጋዛን አንለቅም” ያሉት የጋዛ ነዋሪ ፍሊስጤማውያን፤ “የትራምፕን ውሳኔ እንቃወማለን፣ ጦርቱን አስቁሟል፤ ነገር ግን እኛን ማፈናቀል ህይወታችን እንዲያበቃለት ያደርጋል” ብለዋል።
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምት መደረሱን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍሊስጤማውያን ወደ ፈራረሰቸው መንደራቸው እየተመሙ ይገኛሉ።
እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ከሆነ ከአጠቃላይ የጋዛ ነዋሪዎች መካከል 1.9 ሚሊየን ወይም 90 በመቶው በ15 ወሩ ጦርት ከመኖሪያቸው ለመፈናቀል ተገደዋል።