ሳኡዲ አረቢያ የሀጅ ተጋዦችን የተመለከተ አዲስ ጥብቅ መመሪያ አወጣች
ሚኒስቴሩ የህዝብን ሰላም እና ደህንነት ለማናጋት አስቦ ወደ ሳኡዲ የሚገባ እንደሚባረር አስጠንቅቋል
አዲሱ መመሪያ አመታዊው የሀጅ ጉዞ ለፖለቲካ አላማ እና ለሃይማኖታዊ ክፍፍል ጥቅም ላይ እንዳይውል በጥብቅ ይከለክላል
ሳኡዲ አረቢያ የሀጅ እና ኡምራህ ሚኒስቴር የሀጅ ተጋዦችን የተመለከተ አዲስ ጥብቅ መመሪያ ማውጣቱን አስታወቀ።
የሳኡዲ አረቢያ የሀጅ እና ኡምራህ ሚኒስቴር አመታዊውን የሀጅ ጉዞ ለፖለቲካ እና ለሀይማኖታዊ ክፍልል ጥቅም ላይ እንዳይውል ለማድረግ አዲስ ጥብቅ መመሪያ ማውጣቱን አስታውቋል።
ሚኒስቴር የህዝብን ሰላም እና ደህንነት ለማናጋት አስቦ ወደ ሳኡዲ የሚገባ እንደሚባረር አስጠንቅቋል።
በአዲሱ ረቂቅ መመሪያ መሰረት ሁሉም የውጭ የሀጅ ቢሮዎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። እነዚህ ቢሮዎች ካሉባቸው ሀገራት ለሚመጡ የሀጅ ተጋዦች ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው እና ሚኒስቴሩ ያወጣቸውን ትዕዛዞች እና መመሪያዎች ማክበር እንዳለባቸው ተገልጿል።
ቢሮዎቹ ተጓዦቹ ከመድረሳቸው በፊት የተጓዦቹን መረጃ ወደ ኤሌክትሪክ ስርአት ማስገባት እና ተጓዦቹ የፖለቲካ ፍላጎት የሌላቸው እና ብጥብጥ የማይፈጥሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው በመመሪያው ተጠቅሷል።
ከዚህ በተጨማሪም መመሪያው ቢሮዎቹ ለሀጅ ተጓዦች የቀረቡ ትራንስፖርት አማራጮችን እና ሆቴሎችን ሳይፈቅድላቸው ከመጠቀም እንዲቆጠቡ እንዲሁም ከሀጅ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ የንግድ ወይም የድለላ ተግባር ላይ እንዳይሰማሩ ይከለክላል።
ሚኒስቴሩ ሀጅ ለሀይማኖታዊ ክፍፍል ወይም የፖለቲካ ፍጆታ ጥቃም ላይ እንዳይውል ለመከላከል ቁርጠኛ መሆኑን እና ችግር በሚፈጥሩት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።
እንደ መመሪያው ከሆነ ሚኒስቴሩ በጥፋት የተሳተፉ የቢሮ ኃላፊዎችን ወይም ስራተኞችን ከሀገር ያባርራል፤ በቂ ሆኖ ካለገኘው ደግሞ በሌሎች የሀጅ ጉዞዎች ወቅት የሚኖሩ የቢሮ ሰራተኞችን ቁጥር ይቀንሳል።
መመሪያው ለውጭ የሀጅ ቢሮዎች እውቅና ለመስጠት የፍቃድ ጥያቄ መቅረቡን፣ ሰራቶች ብቁ መሆናቸውን መረጋገጡን እና ከሚኒስቴሩ የኤሌክትሪክስ ሲስተም ጋር መያያዙን ጨምሮ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል።
ሚኒስቴሩ በኤክስ ገጹ እንዳስታወቀው አዲስ መመሪያ ማውጣት ያስፈለገው በዓሉ በሚከበርበት ወቅት መጨናነቅን ለማስወገድ እና ኡምራህን በሰአቱ ለማከናወን ነው።