በኒዮርክ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሴቶች ስብሰባ ላይ ሶማሊያዊን በወንድ መወከላቸውን ተቃወሙ
ሶማሊያ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የሴቶች ሚኒስትርን በማፍረስ ስሙን ቀይራለች
በተመድ አዘጋጅነት በተካሄደው የሴቶች ጉባኤ ላይ ሶማሊያ በቤተሰብ እና ሰብዓዊ ሚኒስትሩ በጀነራል ባሽር መሀመድ ተወክላለች
በኒዮርክ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሴቶች ስብሰባ ላይ ሶማሊያዊን በወንድ መወከላቸውን ተቃወሙ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሴቶች ጉዳይ በኒዮርክ ከተማ የአባል ሀገራት ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
57 ሀገራት በተሳተፉበት በዚህ ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ነች፡፡
የሶማሊያ ቤተሰብ እና ሰብዓዊ መብት ሚኒስትሩ ጀነራል ባሽር መሀመድ ስለ ሴቶች በሚመክረው በዚህ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን የሚያሳይ ምስል በኤክስ ወይም በቀድሞ ስሙ ትዊተር ገጽ ላይ ማጋራታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ በመላው ሶማሊያ ትኩረት ስቧል፡፡
ሶማሊያዊያን በሴቶች ጉባኤ ላይ እንዴት በወንድ እንወከላለን ሲሉ ክስተቱን የተቹ ሲሆን ወትሮም ቢሆን የሶማሊያ መንግስት ለሴቶች ግድ የለውም ብለዋል፡፡
የሶማሊያ መንግስት ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የሴቶች ሚኒስቴርን በማፍረስ ወደ ቤተሰብ እና ሰብዓዊ መብት ሚኒስቴር ቀይሯል፡፡
በሰሜን ሶማሊያ የአይኤስ ታጣቂዎች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩ ተነገረ
ይህን ተከትሎ በርካታ ሶማሊያዊያን የአሁኑን ክስተት ካለፈው ጋር በማያያዝ መንግስታችን ሴቶች የሚለውን ቃል መጥራትም አይፈልግም ሲሉ ከሰዋል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ያለው ነገር ባይኖርም ሁለት ሴቶች ለዚሁ ጉባኤ ሲባል ወደ ኒዮርክ ከሄደው የሶማሊያ ልዑክ ጋር ማቅናቸውን የሚሳዩ ፎቶዎች ቀስ በቀስ መውጣት ጀምረዋል፡፡
በተመድ የሴቶች ጉባኤ ላይ ከ57 ሀገራት የተውጣቱ 197 ሰዎች እየተሳተፉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 21 ወንዶች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡