975ኛ ቀኑን ባስቆጠረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምን አዳዲስ ክስተቶች ተመዝግበዋል?
የሩሲያ ጦር ቁልፍ የሆነችውን የዩክሬኗ ፖክሮቭስ ከተማን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ ነው
የዩክሬን የአየር መከላከያ ዩኒት በርካታ የሩሲያ ድሮኖችን አየር ላይ አምክኛለሁ ብሏል
በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ዛሬ 975ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፤ ውጊያ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የሩሲያ ጦር በዩክሬን በተለይም በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል የተለያዩ አካባዎችን እየለያዩ አካባዎችን እየተቆጣጠረ ወደ ፊት እየገሰገሰ መሆኑ ተነግሯል።
የሩሲያ ጦር የተለያዩ መንደሮችን መያዙም ቁልፍና ስትራቴጂክ የሆነችውን የዩክሬኗ ፖክሮቭስ ከተማን ለመያዝ ያለው ግስጋሴ እንዲፋጠን አድርጎታል።
በሁለቱም ወገኖች በድሮን እና በሚሳዔል የሚፈጸሙ ጥቃቶችም የቀጠሉ ሲሆን፤ የዩክሬን የአየር መከላከያ ዩኒት በርካታ የሩሲያ ድሮኖችን አየር ላይ አምክኛለሁ ብሏል።
በዛሬው እለት ጠዋት ላይ ሩሲያ የዩክሬኗን ኪቭ ኢላማ ያደረጉ በርካታ ድሮኖችን መላኳም የተገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ በርካቶችምመ አየር ላይ ማምከኗን ነው ዩክሬን ያስታወቀችው።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴርም እስከ እሁድ ጠዋት ድረስ ከዩክሬን የተነሱ ከ30 በላይ የድሮን ጥቃቶችን አምክኛለሁ ብሏል።
የድሮን ጥቃቶቹ በቮሮኔዝ ደቡባዊ ክልል የምትገኘውን ቮሮኔዝ ክልልን ኢላማ ያደረገ ሲሆን፤ በዩክሬን የድሮን ጥቃት አንድ ሴት ስትቆስል የተወሰኑ መኪኖችም መውደማቸውን የከተማዋ ከንቲባ አስታውቀዋል።