የኢምሬትስ እና ሳኡዲ መሪዎች ሩሲያና አሜሪካን ማደራደራቸው ተገለጸ
ሩሲያ እና አሜሪካ የእስረኛ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የማደራደር ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል
ሩሲያ እና አሜሪካ በዛሬው ዕለት ሁለት ተጽዕኖ ፈጣሪ እስረኞችን ተለዋውጠዋል
የአረብ ኢምሬትስ እና ሳውዲ አረቢያ መሪዎች ሩሲያን እና አሜሪካንን ማደራደራቸው ተገለጸ።
አሜሪካ እና ሩሲያ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ሳውዲ አረቢያ መሪዎች አደራዳሪነት የአንድ ለአንድ እስረኞችን ተለዋውጠዋል።
ሩሲያ ታዋቂዋ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቿን ብሪትኒ ግሪነር በአደገኛ እጽ ዝውውር ወንጀል ተጠርጥራ ላለፉት ዓመታት በሞስኮ ባለ እስር ቤት ነበረች።
አሜሪካም ሩሲያዊው ቪክቶር ቦትን በህገ ጦር መሳሪያ ንግድ እና ዝውውር ወንጀል ተጠርጥሮ በተመሳሳይ እስር ላይ እንደነበር ተገልጿል።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ እና የሳውዲው አቻቸው መሀመድ ቢን ሰልማን በጋራ በመሆኑ አሜሪካ እና ሩሲያ የእስረኞች ልውውጥ እንዲያደርጉ ማደራደራቸውን የሁለቱ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም የአረብ ኢምሬትስ እና ሳውዲ አረቢያ መሪዎች ላደረጉት ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አሜሪካንን በሁለት የኦሎምፒክ ውድድር ላይ በመወከል ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣችው ግሪነር ከእስር መለቀቋ አሜሪካዊያንን አስደስቷል ተብሏል።
አሜሪካ በዓለም የጦር መሳሪያ ንግድ ዋነኛ ሸሪክ እንደሆነ በሚጠቀሰው ሩሲያዊው ቪክቶር ቦት ላይ የ25 ዓመት እስር ወስናበት ነበር።
ሩሲያ ለብሔራዊ ጥቅሟ ስትል በጥብቅ የምትፈልገው ቪክቶር ቦት ከዋሸንግተን እስር ተለቆ በእጇ መግባቱን አረጋግጣለች።