ሳዑዲ አረቢያ መንግስት “ለሳዑዲ ህዝብ እሴቶች የማይመጥን ቀለም አላቸው” የተባሉ እቃዎችን እያሰወገደ ነው
የሳዑዲ መንግስት ግብረሰዶምን ያበረታታሉ በሚል አሻንጉሊቶችን ጨምሮ የቀስተ ደመና ቀለም ያላቸው እቃዎችን እየሰበሰበ ነው
የቀስተ ደመና ቀለም ያላቸው እቃዎች በሳዑዲ መንግስት ከገበያ ላይ እየተለቀሙ ነው
የሳዑዲ አረቢያ ባለስልጠናት “ለሳዑዲ ህዝብ እሴቶች የማይመጥን ቀለም አላቸው” ያሉዋቸውን ባለቀስተ ደመና ቀለም እቃዎች ከሱቆች እያስወገዱ እንደሆነ ተገለጸ።
በዚህም በርካታ የቀስተ ደመና ቀለም ያላቸው እቃዎች በሪያድ ከሚገኙ በርካታ ስቆች መወገዳቸው የሀገሪቱ ቴሌቭዥን አል-ኤክባሪያ ዘግቧል፡፡
አሻንጉሊቶች ፣የጸጉር ማስያዣ፣ ማሊያዎች፣ ኮፊያ፣ እና የእርሳስ መያዣወች ግብረሰዶምን የሚያበረታታ የቀስተ ደመና ቀለም አላቸው በሚል ከየሱቁ እና መሰጫ መደብሮች እንዲለቀሙ ከተደረጉ እቃዎች ተጠቃሽ ናቸው።
እቃዎቹ " የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነውን ማህበረሰብ ሞራልና እሴት የሚጻረሩ እንዲሁም አዲሱን ትውልድ ለግብረሰዶምነትን የሚያበረታቱ ቀለሞች ያልዋቸው ናቸው" ሲሉም ነው አንድ ከፍተኛ የሳዑዲ ባለስልጣን የገለጹት።
የሀገሪቱ የንግድ ሚኒሰቴር በበኩሉ እቃዎቹን እንዲያስወግዱ በከተማው ያሰማራቸው አባላቱ ዋና ትኩረት "ለሳውዲ ህዝብ እሴቶች የማይመጥን ቀለም ያላቸው እቃዎች " ማስወገድ መሆኑ በትዊተር ገጹ ባጋራው ጽሁፉ አስታውቋል።
መሰል እቃዎች ሲሸጡ በሚገኙ ሱቆች ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም ሚኒሰቴሩ አስጠንቅቋል።
እንደ ሳዑዲ ሁሉ ኳታር ባሳለፍነው ወርሃ ታህሳስ “እስላማዊ እሴቶች ሚጻረር መልእክት አላቸው ያለቻቸው” ባለ ቀስተ ደመና ቀለም እቃዎች ከንግድ ቤቶች እንዲወገዱ ማድረጓ ሚታወስ ነው።
የሱኒ ሙስሊሞች ሀገር እንደሆነች የሚነገርላት ሳዑዲ አረቢያ፤ ያልተገባ ጾታዊ ግንኙነት የሚከለክል የሚታወቅ ህግ ባይኖራትም የግብረሰዶማዊነትን ግን አትፈቅድም።
በእስላማዊ ህግ አተረጓጎምም መሰረትም ፤ ሀገሪቱ ግብረሰዶም ናቸው አድርገዋል ባለቻቸው ዜጎች እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ስትበይን ቆይታለች።