ሳዑዲ አረቢያ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ምክክር አካሄደች
የሳዑዲ ንጉሳዊ ም/ቤት አማካሪ አህመድ ቢን አብዱላዚዝ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል
አህመድ ቢን አብዱላዚዝ ጠ/ሚ ዐቢይን ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት ጋር ተመካክረዋል
የሳዑዲ አረቢያ ንጉሳውያን ምክር ቤት አማካሪ አህመድ ቢን አብዱላዚዝ ካንታን በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው ተነግሯል።
አህመድ አብዱላዚዝ ካንታን በአዲስ በባ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተገናኘት መምከራቸው አል ዐይን ከኤምባሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የሳዑዲ አረቢያ ንጉሳውያን ምክር ቤት አማካሪው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታም በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም በዓለማቀፋዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ታውቋል።
አህመድ ቢን አብዱላዚዝ ካንታን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ቡርቱካን አያኖ ጋር ተገናኝተውም ተወያይተዋል።
በነባራቸው ቆይታም በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች እንዲሁም ግንኙነቶች ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ነው የተባለው።
በውይይቶቹ ላይም በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ፈሃድ ኦባይዶላህ አል ሁምዳኒ እና ካውስለር ፈረሃን አል ፈርሃን ተገኝተዋል።
የሳዑዲ አረቢያ ንጉሳውያን ምክር ቤት አማካሪ አህመድ ቢን አብዱላዚዝ በተለያዪ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተነግሯል።
ይህ የአፍሪካ ጉብኝታቸው ለ5ኛ ጊዜ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ፣ ዚምባብዌ እና ኬፕቨርዴ የጉዟቸው አካ እንደሆነም ነው የተገለፀው።