ቻይና በሳኡዲ አረቢያ በዩክሬን ጉዳይ በሚደረገው ንግግር ላይ ልትሳተፍ ነው
ቻይና፣ ሳኡዲ አረቢያ በዩክሬን ጉዳይ ባዘጋጀችው ንግግር ላይ የሚሳተፍ ልዩ መልእክተኛ ልትልክ መሆኑ ተገልጿል
በታቀደው ንግግር ላይ ዩክሬን የተጋበዘች ሲሆን ሩሲያ ግን አልተጋበዘችም
ቻይና፣ ሳኡዲ አረቢያ በዩክሬን ጉዳይ ባዘጋጀችው ንግግር ላይ የሚሳተፍ ልዩ መልእክተኛ ልትልክ መሆኑ ተገልጿል።
በታቀደው ንግግር ላይ ዩክሬን የተጋበዘች ሲሆን ሩሲያ ግን አልተጋበዘችም።
የሩሲያ መንግስት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ከሳምንት በፊት በጉዳዩ ዙሪያ ተጠይቀው ሩሲያ የንግግሩ አለማ ምን እንደሆነ ማወቅ እንደምትፈልግ ተናግረዋል።
ቻይና በትናንትናው እለት እንዳስታወቀችው ለዩክሬን ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ በሳኡዲ አረቢያ በሚካሄደው ንግግር ላይ የሚሳተፍ ልዩ መልእክተኛ ትልካለች።
ይህ ምዕራባውያን ሀገራት የሚሳተፉበት እና ሩሲያን ያላሳተፈው ንግግር ለዩክሬን የዲፕሎማሲ ትርፍ ሊያስገኝ እንደሚችል ተጠብቋል።
የዩክሬን እና ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ከ40 በላይ ሀገራት ዲፕሎማቶች የሚሳተፉበት የሳኡዲ አረቢያው ንግግር የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትን በሰላም ለመፍታት በቁልፍ መርሆች ላይ ስምምነት ላይ ይደርሳል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል።
ቀደም ሲል ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የሚደረግ የሰላም ንግግርን እንደማትቃወሞ ገልጸው ነበር።
ነገርግን ዩክሬን የጀመረችው መጠነ ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ሳይቆም የሰላም ንግግር ሊኖር እንደማይችል ተናግረዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በአንጻሩ ሩሲያ በወረራ የያዘችውን የዩክሬን ግዛት ሳትለቅ ንግግር የማይታሰብ ነው ሲሉ መናገራቸው ይታውሳል።