ተመራማሪዎች ሆዳችን እንደጠገበ ለአዕምሮ በስህተት የሚናገር ቴክኖሎጂ ፈጠሩ
አዲሱ ቴክኖሎጂ ምግብ እንደተበላ እና ሆዳችን ሙሉ እንደሆነ ለአዕምሮ የተሳሳተ መልዕክት የሚልክ ነው ተብሏል
ቴክኖሎጂው ክብደታቸውን መቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች ጥሩ ምርጫ እንደሚሆን ተገልጿል
ተመራማሪዎች ሆዳችን እንደጠገበ ለአዕምሮ በስህተት የሚናገር ቴክኖሎጂ ፈጠሩ፡፡
በዓለማችን ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በየጊዜው እየዘመነ ሲሆን አሁን ደግሞ የሰው ልጆች አዕምሮ የምግብ መመገብ ፍላጎትን የሚቀንስ ፈጠራ መሰራቱ ተገልጿል፡፡
ቴክኖሎጂው አዕምሯችን ምግብ ሲያስፈልገው የረሃብ ስሜትን በመፍጠር ምግብ እንድንመገብ ይደረግ የነበረውን ተፈጥሯዊ ኡደትን በማስተጓጎል የሰው ልጆችን የምግብ ፍላጎት እንዲቀንስ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
በሀርቫርድ ዩንቨርሲቲ የባዮኢንጅነሪንግ ተመራማሪዎች ተሰራ የተባለው ይህ ቴክኖሎጂ ለአዕምሯችን የተሳሳተ መልዕክት ማለትም በሆዳችን ውስጥ አሁንም ምግብ እንዳለ በመንገር ተጨማሪ ምግብ የመመገብ ፍላጎት እንዳይኖረን ያደርጋል፡፡
ሕይወትን ያለ ገንዘብ እና ቴክኖሎጂ የሚኖረው ሰው
ይህ ቴክኖሎጂ በአሳማ ላይ ተሞክሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ሲሆን እስከ 40 በመቶ የአሳማዎች የመመገብ ፍላጎት እንደቀነሰ ተገልጿል፡፡
ይህ ፈጠራ በተለይም ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች ጥሩ ምርጫ ይሆናል የተባለ ሲሆን እንክብል መድሃኒቶቹን በመዋጥ በጨጓራችን ውስጥ የጥጋብ ስሜትን እንዲያመነጩ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
ቫይብ እንክብል የተሰኘው ይህ መድሃኒት የተለመደ የመመገቢያ ሰዓታችን ከመድረሱ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ ይወሰዳል የተባለ ሲሆን መጠኑ የቫይታሚን መድሃኒት ጋር ተመሳሳይ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
ይህ እንክብልም የጥጋብ ስሜት ከጨጓራ ወደ አዕምሮ ከላከ በኋላ እንደ ማንኛውም የሰውነታችን አላስፈላጊ ነገር እንዲወገድ ሆኖ የተሰራ ነው ተብሏል፡፡
ይሁንና መድሃኒቱ ለተጠቃሚዎች ወደ ገበያ ከመቅረቡ በፊት በስነ ልቦና ረገድ ሊያደርሰው የሚችለው ተጽዕኖ ዙሪያ በቀጣይ ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልገው የጥናቱ አካል እና በበርሚንግሀም ዩንቨርሲቲ የሆድ እቃ ተመራማሪው ጆቫኒ ተርቬርሶ ለሳይንስ ጆርናል መጽሄት ተናግረዋል፡፡