ኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስን ከሰውነት ውስጥ ማስወገድ መቻላቸውን ተመራማሪዎች ተናገሩ
አዲሱ ግኝት የቫይረሱን ህዋስ ቆርጦ ማውጣት የሚያስችል ነው ተብሏል
ምርምሩ በበጎ ፈቃደኞች ላይ ተሞክሮ ስኬታማ እንደሆነም ተገልጿል
ኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስን ከሰውነት ውስጥ ማስወገድ መቻላቸውን ተመራማሪዎች ተናገሩ፡፡
የሆላንዱ አምስተርዳም ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች እንደገለጹት የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ህዋስን ከሰውነት ውስጥ ማጥፋት መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ አክለውም የቫይረሱን ህዋስ ከሰውነታችን ውስጥ በመቁረጥ አልያም ህይወት አልባ እንዲሆን ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ አዲሱ ፈጠራ ከዚህ በፊት ጂን በመቁረጥ አንድን ህዋስ ከሰውነታችን ውስጥ ማስወጣት አልያም ህይወት አልባ ማድረግ ይቻላል በሚል በጤና ዘርፍ የኔቬል ሽልማትን ያሸነፈውን ፈጠራ መነሻ በማድረግ አሁን በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ ተሞክሮ ውጤታማ ሆኗል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ “በቀን በአማካኝ 30 ሰዎች በኤድስ ህይወታቸው ያጣሉ” ተባለ
በዚህ ፈጠራ አማካኝነት የዓለማችን ገዳይ በሽታ ከሆኑት ውስጥ ዋነኛው የሆነውን ኤችአይቪ ኤድስን ቫይረስን ለማጥፋት እንደሚቻል ትልቅ ተስፋ ሰጥቷል፡፡
አዲሱ ፈጠራ በሶስት የቫይረሱ ተጠቂዎች ላይ ተሞክሮ ውጤታማ ሆኗል የተባለ ሲሆን ለ48 ሳምንታት በተደረገው የህክምና ሙከራ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት አልታየባቸውም ተብሏል፡፡
በኖቲንግሃም ዩንቨርሲቲ የስቲም እና ጅን ቀዶ ህክምና ሐኪሙ ዶክተር ጄምስ ዲክሰን እንዳሉት አዲሱ ፈጠራ ቫይረሱን ከሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ማስወገድ እንደሚቻል ለማረጋገጥ ተጨማሪ ምርምሮች እንደሚስፈልጉ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊት የነበሩት የጸረ ኤችአይቪ ኤድስ መድሀኒቶች ቫይረሱ እንዳይስፋፋ የሚያደርጉ እንጂ ፈዋሽ አይደሉም ተብሏል፡፡
ላለፉት በርካታ ዓመታት ኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስን ለማጥፋት በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ሲሆን እስካሁን ድረስ ለቫይረሱ ፈዋሽ መድሃኒት አልተገኘለትም፡፡