አሜሪካ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ ክትባቶችን ለዜጎቿ ልትሰጥ ነው
ይህ በቫይረሱ የ38 ዓመታት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነ ነው
የሃገሪቱ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ክትባቶቹ እንዲሰጡ አዟል
አሜሪካ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ ክትባቶችን ለዜጎቿ ልትሰጥ ነው፡፡
በገዳይነቱ 38 ዓመታትን ያስቆጠረው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በአገረ አሜሪካ ቫይረሱን መከላከል የሚያስችል ክትባት እንደተገኘለት ተገልጿል፡፡
ቫይረሱ በዓለም ዙሪያ 37 ሚሊዮን ሰዎችን የገደለ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 25 ሚሊዮን ያህሉ አፍሪካዊያን ናቸው።
የአሜሪካ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳድር እንዳሳወቀው ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ከዚህ ቫይረስ መጠበቅ የሚያስችል ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ ለዜጎች እንዲሰጥ አጽድቋል፡፡
‘አፕሪቱድ’ ወይም ‘ካቦቲግራቪየር’ የተሰኘው ይህ ክትባት በተለይም ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ እና ከ35 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ላላቸው ወጣቶች እንዲሰጥ አሜሪካ አጽድቃለች፡፡
ክትባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ወር ውስጥ ሁለት ጊዜ ለተጋላጭ ወጣቶች ከተሰጠ በኋላ በየሁለት ወሩ እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን ይህ ክትባት በተለይም በየእለቱ የእንክብል መድሃኒትን መውሰድ ለማይችሉ ጥሩ መፍትሄ ይሆናል መባሉን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
በፈረንጆቹ 2030 ከኤችአይቪ ኤድስ ነጻ የሆነች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው
በዓለማችን ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ትሩቫዳ የተሰኘ የጸረ ኤች አይ ቪ ኤድስ እንክብል መድሃኒት በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
ይህ መድሃኒት ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ እና ተመርምረው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ከታወቀ በኋላ በየእልቱ በእንክብል መልኩ ይሰጣል፡፡
በአሜሪካ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳድር የጸደቀው አዲሱ ክትባት በየእልቱ በእንክብል መልኩ ይሰጥ የነበረውን መድሃኒት በየሁለት ወሩ በመርፌ መልኩ የሚሰጥ ነው፡፡
“የኮሮና ወረርሽኝ የኤች አይ ቪ ምርመራዎች በ41 በመቶ እንዲቀንሱ አድርጓል”- ጥናት
ይህ አዲስ ጸረ ኤድስ ክትባት በ13 አገራት ላይ ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ ወጣቶች በሙከራ ደረጃ ተሰጥቶ በእንክብል መልኩ ሲሰጥ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር 90 በመቶ ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዓለማችን በየዓመቱ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች በኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ የሚያዙ ሲሆን በ2020 ዓመት ብቻ ከ680 ሺህ በላይ ዜጎች በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡