ሳይንቲስቶች 99 በመቶ የወባ ትንኝትን ንክሻ የሚከላከል መድሃኒት ፈጠሩ
መድሃኒቱ የወባ ትንኝ የሰው ልጆችን ጠረን መለየት እንዳትችል የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል
ምርምሩን የሰሩት የእስራኤል ተመራማሪዎች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ መድሃኒቱን ለገበያ እናቀርባለን ብለዋል
ሳይንቲስቶች 99 በመቶ የወባ ትንኝትን ንክሻ የሚከላከል መድሃኒት ፈጠሩ፡፡
የወባ በሽታ በዓለማችን በሰው ልጅ ገዳይነቱ ከሚታወቅ ሲሆን እስካሁን ሙሉ ለሙሉ የሚያጠፋ መድሃኒት አልተገኘለትም፡፡
በሽታው በወባ ትንኝ ንክሻ አማካኝነት የሚፈጠር ሲሆን ከወደ እስራኤል መፍትሄ መገኘቱን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ የእስራኤል ሳይንቲስቶች 99 በመቶ የወባ ትንኝ በሰው ቆዳ ላይ እንዳያርፉ እና ንክሻ እንዳይፈጥሩ የሚያደርግ መድሃኒት ፈጥረዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ በቆዳ ለይ የሚቀባ ኬሚካል የፈጠሩ ሲሆን ይህ ኬሚካል የወባ ትንኝ በሰው ቆዳ ላይ እንዳታርፍ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
በሂብሪው ዩንቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ጆናታን ባህቦት እንዳሉት ኬሚካሉ በሰው ልጆች ቆዳ ላይ ሲቀባ የወባ ትንኝ የሰው ልጅን ጠረን መለየት እንዳትችል እና በሰዎች ቆዳ ላይ እንዳታርፍ የሚያደርግ ነው፡፡
የወባ ትንኝ በሰው ቆዳ ላይ እንዳታርፍ የሚያደርገው ኬሚካል በአበባዎች ላይ ከሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን ልዩ ስሙም ሴሉሎስ እንደሚባል ተመራማሪዎቹ ገልጸዋልል፡፡
ይህ ኬሚካል ለዓመታት በሙከራ ለይ ቆይቷል የተባለ ሲሆን 99 በመቶ ውጠየታማነቱ መረጋገጡም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ተመራማሪዎቹ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ መድሃኒቱን ለሸማቾች ወደ ገበያ እንደሚያቀርቡትም አስታውቀዋል፡፡