የድምጽ ብክለት ሴቶችን የበለጠ ለመካንነት እንደሚዳርግ ተመራማሪዎች ተናገሩ
አምስት ዓመት እና ከዛ በላይ የአየር ብክለት ባለበት አካባቢ ከኖሩ ለመካንነት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ይሆናልም ተብሏል
900 ሺህ ሰዎች በተሳተፉበት በዚህ ጥናት ላይ ሴቶች የበለጠ ለመካንነት ተጋልጠው ተገኝተዋል
የድምጽ ብክለት ሴቶችን የበለጠ ለመካንነት እንደሚዳርግ ተመራማሪዎች ተናገሩ፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ የሰው ልጆችን ህይወት በእጅጉ እየፈተኑ ካሉ ክስተቶች መካከል አንዱ ሲሆን ጉዳቱ ደግሞ በቀላሉ የማይቀለበስ እና ዘላቂ ነው፡፡
የብሪታንያው ሜዲካል ጆርናል ይፋ እንዳደረገው ጥናት ከሆነ የድምጽ ብክለት ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ለመካንነት የተጋለጡ ናቸው ብሏል፡፡
በዴንማርክ 900 ሺህ ገደማ ሰዎች በተሳተፉበት በዚህ ጥናት ላይ የድምጽ ብክለትን ጨምሮ የተበከለ አየር ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ለመካንነት ችግር ተጋልጠው ተገኝተዋል፡፡
እድሜያቸው ከ30 እስከ 45 ዓመት የሚሆናቸው ሴቶች ላይ የድምጽ ብክለት የበለጠ ለመካንነት ይዳርጋቸዋል ተብሏል፡፡
ወንዶችን ለመካንነት የሚዳርጉ ምክንያቶችን ያውቃሉ?
የአየር ንብረት ለውጥ የወንዶችን የወንድ ዘር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ ለመካንነት ይዳርጋል መባሉ ከዚህ በፊት ይፋ የተደረገ ቢሆንም ሁካታ እና ወከባ ባለባቸወ አካባቢዎች መኖር ለመካንነት ያጋልጣል ሲባል የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የድምጽ ብክለት ከሴቶች በተጨማሪም ወንዶችንም ለመካንነት ይዳርጋል የተባለ ሲሆን በተለይም እድሜያቸው ከ37-45 ዓመት ያሉት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ተብሏል፡፡
በጥናቱ ከተሳተፉት መካከልም 16 ሺህ ወንዶች እንዲሁም 22 ሺህ 600 ያህሉ ሴቶች ለመካንነት ተጋልጠው ተገኝተዋል ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የተሽከርካሪዎች ድምጽ፣አቧራ እና የፋብሪካዎች ድምጽ ለመካንነት ከሚያጋልጡ የድምጽ ብክለቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸውም ተብሏል፡፡
የተጠቀሱት ብክለቶች በወንዶች ላይ የወንዴ ዘር ፍሬ መጠን እንዲቀንስ በማድረግ መካንነትን ያስከትላል የተባለ ሲሆን በሴቶቹ ላይ እንዴት መካንነትን እንደሚያደርስ በጥናቱ ላይ አልተጠቀሰም፡፡