በአለም ትልቁ የኢቨረስት ተራራ እያደገ መሆኑን ሳይቲስቶች ገለጹ
ከባህር ወለል በላይ 8.85 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የአለም ትልቁ የኢቨረስት ተራራ እስካሁን እያደገ ነው።
ሳይንቲስቶች የእድገቱን ምክንያት ባቅራቢያው ያሉ ሁለት ወንዞች መጋጠም ነው ይላሉ
በአለም ትልቁ የኢቨረስት ተራራ እያደገ መሆኑን ሳይንቲስቶች ገለጹ።
ከባህር ወለል በላይ 8.85 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የአለም ትልቁ የኢቨረስት ተራራ እስካሁን እያደገ ነው።
ኢቨረስት እና ሌሎች የሂማሊያ ቦታዎች የህንድ ከፊል አህጉር ከኢዩራዥያ ጋር ተጋጭቶ ከተፈጠረበት ከዛሬ 50 ሚሊዮን አመታት በፊት ጀምሮ ከተጠበቀው በላይ በማይቆም እድገት ላይ ነው። አሁን ላይ ሳይንቲስቶች የእድገቱን ምክንያት ምን እንደሆነ አውቀነዋል ብለው ያስባሉ፤ ባቅራቢያው ያሉ ሁለት ወንዞች መጋጠም ነው ይላሉ።
የኮሲ እና የአሩን ወንዞች ከ89 ሺ አመታት በፊት ወደ አንድ መግጠማቸው የቀጠናው የወንዝ ስርአት በመቀየሩ ኢቨረስት 15-50 ሜትር እንዲያድግ አድርጎታል። ይህ ማለት ተራራው በየአመቱ ከ0.2-0.5 ሜትር ድረስ ያድጋል ማለት ነው።
ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት ይህ የዲኦሎጂካል ሂደት "አይሶስታቲክ ሪባውንድ" ይባላል። ይህ የመሬት ገጸ ምድር ክብደት ሲቀንስ የመሬት ቅርፊት( የመሬት የላይኛው ክፍል) ወደ ላይ ከፍ እንዲል ያደርጋል።
የመሬት ቅርፊት በከፊል ፈሳሽ ከሆነ አለት ላይ ተንሳፎ የሚገኝ ነው። የኮሲ ወንዝ የአሩን ወንዝን በመዋጥ መንገድ ሲቀይር ከፍተኛ መጠን ያለውን አፈር እና አለት ጠራርጎ በመውሰዱ ኢቨረስት እና በአካባቢው ያለው ክብደት ቀንሷል።
"አይሶስታቲክ ሪባውንድ ማለት በመንሳፈፍ ላይ ያለ ቁስ ክብደት ሲቀንስ ቦታ እንደሚቀይረው ማለት ነው" ሲሉ በቤጂንግ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የቻይና የጂኦሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ጂኦሳይንቲስት ጂን ጀን ዳይ ሰኞ በታተመው 'ኔቸር ጂኦ ሳይንስ ጆርናል' ላይ ተናግረዋል።
"እንደ በረዶ ያሉ ከባድ ክብደቶች ወይም የተሸረሸሩ አለቶች ከመሬት ቅርፊት ሲወገዱ፣ ውሃ ላይ ያለች ጀርባ ጭነት ሲነሳላት ከፍ እንደምትለው ሁሉ መሬቱም ቀስ እያለ ወደ ላይ ይነሳል" ይላሉ ዳይ። የሁለቱ ወንዞች የተቀላቀሉት ከኢቨረስት ተራራ በስተምስራቅ በኩል 45 ኪሎሜት ላይ ነው።
የወንዝ ስርአቱን አመጣጥ ለማሳየት ኑሜሪካል ሞዴል የተጠቀሙት ተመራማሪ አይሶስታቲክ ሪባውንድ ለተራራው አመታዊ እድገት 10 በመቶ አስተዋጽእ እያደረገ ነው። ይህ የጂኦሎጂካል ሂደት በሂማሊያ ብቻ የተፈጠረ አይደለም።
"በስካንዲኒቪያን በበረዶ ዘመን ቀጣናውን የሸፈነው የበረዶ ክምር ሲቀልጥ የመሬት ቅርፊት ወደ ላይ ከፍ እያለ ነው። ይህ ሂደት እስከዛሬ ድርስ መቀጠሉን እና በጠረፍ አካባቢ ባሉ ቦታዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው" ብለዋል ዳይ።
የጥናቱ ተባባሪ የሆኑት የለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በኧርዝ ሳይንስ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ የሆኑት አዳም ስሚዝ የጂፒኤስ መለኪያዎች ኢቨረስት እና ሌሎች የሂማሊያ ቦታዎች እያደጉ መሆናቸው እንደሚያሳዩ ተናግረዋል።