በሴራሊዮን መዲና በነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር 99 ደረሰ
የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችልም ይገመታል
የሴራልዮን ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳ ባዮ ለሟቾች ቤተሰብ መጽናናትን ተመኝተዋል
በሴራሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታውን በነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 99 ሰዎች ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጠናት አስታወቁ፡፡
የሴራልዮን የማእከላዊ ግዛት አስከሬን ክፍል ስራ አስኪያጅ ከደረሰው ፍንዳታ አንጻር የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ብሏል፡፡
በፍንዳታው የቆሰሉ ከ100 በላይ ሰዎች በተለያዩ ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች የህክምና እርዳታ እያገኙ መሆናቸው የገለጹት ደግሞ የሴራልዮን የጤና ሚኒሰትር ዴኤታ አማራ ጃምባይ ናቸው፡፡
የብሔራዊ አደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ ኃላፊ ብሪማ ቡረህ በበኩላቸው “ በርካታ ጉዳቶች አጋጥሟል፤ የተቃጠሉ አስከሬኖች ሁሉ አሉ፡፡ በጣም ፈታኝ ወቅት ላይ ነን” በማለት የደረሰው አደጋ አስከፊነት በኦንላይ ሚድያ እየተሰራጨ ባለ ቪድዮ ሲናገሩ ተስተውለዋል፡፡
የሴራልዮን ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳ ባዮ "የሚወዷቸውን ላጡ ቤተሰቦች እና በዚህ ምክንያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ጥልቅ ሀዘነ እንደተሰማኝ ለመግለጽ እውዳለሁ" ሲሉ ለሟቾች ቤተሰብ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
መንግስት የተጎዱትን ቤተሰቦች ለመደገፍ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋልም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡ምስሎቹ ማረጋገጥ ባይቻልም በማህበራዊ ሚድያ እና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴወች በመዘዋወር ላይ ያሉ ምስሎች ይህን የሚያሳዩ መሆናቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከሰሃራ በስተደቡብ ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀደም ሲል በታንከር መኪኖች ላይ በደረሱ አደጋዎች የፈሰሰውን ነዳጅ ለመሰብሰብ በቦታው የተሰባሰቡ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።
እንደፈረንጆቹ በ 2019 በታንዛኒያ ምስራቃዊ ታንዛኒያ በደረሰ የቦክ ጫኝ ፍንዳታ 85 ሰዎች እንዲሁም 50 የሚጠጉ ሰዎች በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በ2018 በተመሳሳይ አደጋ ህይዋተቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።
aXA6IDUyLjE0LjguMzQg
ejasoft island