የደቡብ አፍሪካ ተመራማሪዎች “250 ሺህ ዓመታት ያስቆጠረ የሕፃን ራስቅል” አገኙ
ግኝቱ በሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥና ጉዞ ለሚደረጉ ምርምሮች ትልቅ ግብዓት ነው ተብለዋል
ተመራማሪዎቹ ያገኙት ትንሹ ልጅ “የጠፋው” ወይም ሴትዋና ቋንቋ “ሌቲ” የሚል ስም ተሰጥቶታል
ከዊትዋተርስራንድ እና ከሌሎች 13 ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጣው የተመራማሪዎች ቡዱን ከ250 ሺህ ዓመታት በፊት ከአራት እስከ ስድስት አመት እድሜ ባለው ጊዜ ውስጥ የሞተው የአንድ ሕፃን ቅል እና ጥርስ ክፍሎች ማግኘቱን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ የጥልቅ የሰው ዝገመተ ለውጥና ጉዞ ፍለጋ ማዕከል ዳይሬክተርና የቡዱኑ መሪ ሊ ሮጀር በርግር “የሆሞ ናሌዲ ከፊል የራስ ቅል የተገኘው በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በሚገኘው የሰው ልጅ የዓለም ቅርስ ቦታ ላይ ነው” ብሏል፡፡
ሆሞ ናሌዲ ከ335 ሺህ አስከ 236 ሺህ ዓመታት በፊት በመካከለኛው ፕሌይስቶሴን በሚገኝ ዋሻ ውስጥ የተገኘ ጥንታዊ የሰው ልጅ ዝርያ ነው።
እንደፈረንጆቹ በ2013 ለመጀመሪያ ጊዜ ከተገኘ ወዲህ በሁሉም የሆሞ ናሌዲ የሕይወት ደረጃዎች ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ከሁለት ደርዘን በላይ ግለሰቦች ስብርባሪዎች እንዳገኙ የቡዱን መሪ መግለጻቸው ሲጂቲኤን ዘግቧል።
"በዋሻው ውስጥ እንደዚህ ባለ፡ ሩቅ ቦታ ላይ የአንድ ልጅ የራስ ቅል መገኘቱ እነዚህ በርካታ ቅሪቶች በእነዚህ ሩቅ በሆኑ ጨለማ ቦታዎች ውስጥ ምን ያህል እንደሚገኙ እንቆቅልሽ መሆኑ ያመላክታል። በዚህ አስደናቂ መጥፋት ላይ ያለ የሰው ዘመድ የከበበው የብዙዎች ሌላ እንቆቅልሽም አለው” ሲሉም ነው የተናገሩት በርገር።
ቀደም ሲል በአፍሪካ ውስጥ ዘመናዊ ሰዎች ብቻ ናቸው የነበሩ ብለን በምናስብበት ጊዜ የነበረ ጥንታዊ ዝርያ እንደሆነ ግልጽ ነው።
ሮጀር በርግር አክለው “በዚያን ጊዜ እና በዚህ ቦታ መገኘቱ ውስብስብ የድንጋይ መሳሪያ ባህሎችን እና የአምልኮ ስርዓቶችን መፈልሰፍን በተመለከተ ማን ምን እንዳደረገ ያለንን ግንዛቤ ውስብስብ እንዲሆን አድርጎታል”ም ብሏል።
ተመራማሪዎቹ ያገኙት ትንሹ ልጅ በደቡብ አፍሪካ በሚነገር ሴትዋና በተባለው ቋንቋ “የጠፋው” የሚል ትርጉም ያለው “ሌቲ” የሚል ስም ተሰጥቶታል፡፡ስሙ የተሰጠበት ምክንያት ሲያስቀምጡም “የራስ ቅሉ ብቻውን ስለተገኘ እና የአካላቸው ቅሪት ስላልተገኘ ‘ሌቲ’ የሚል ስም ተሰጥቶታል” ብለዋል፡፡