የኢግዚቢሽን አላማ ለኢምሬቶች በ80 ኩባንያዎች 800 የስራ ዕድሎችን መፍጠር ነው ብሏል
የአምራች ኢንዱስትሪዎች ኢግዚቢሽን በአረብ ኢምሬትስ ተከፈተ።
ሁለተኛው የአምራቾች ኢግዚቢሽን በአረብ አምሬትስ በዛሬው እለት ተከፍቷል።
በርካታ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች በጋራ በመሆን ነው ኢግዚቢሽኑን የከፈቱት።
የአረብ ኢምሬትስ ኢንዱስትሪ እና አድቫንስድ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ አድኖክ ግሩፕ፣ ሂማን ሪሶርስ እና ኢምሬታይዜሽን ሚኒስቴር እና ናሽናል ካድሬስ ኮምፒቴቲቭነስ ካውንስል ተባብረው ኢግዚቢሽኑን አዘጋጅተው መክፈታቸውን የአረብ ኢምሬትስ ኢንዱስትሪ እና አድቫንስ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በትዊተር ገጹ አስታውቋል።
ዛሬ የተከፈተው ኢግዚቢሽን አላማው ለኢምሬቶች በ80 ኩባንያዎች 800 የስራ ዕድሎችን መፍጠር ነው ብሏል።
በአቡ ዳቢ እየተካሄደ ያለው ኢግዚቢሽኑ ለሶስት ቀናት ይቆያል ተብሏል።
የመጀመሪያው የአምራቾች ኢግዚቢሽን በርካታ ኢንዱስትሪዎች የተገኙበት እና አበረታች ውጤት የተገኘበት ነበር። በዚህ ኢግዚቢሽን በ73 ኩባንያዎች 500 የሚሆኑ የስራ እድሎችን መፍጠር ተችሎ ነበር።