ፖለቲካ
ደቡባዊ ሴኔጋልን ለመገንጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ትጥቅ ለመፍታት ከመንግስት ጋር ተስማሙ
ታጣቂዎቹ ላለፉት 40 ገደማ ዓመታት ደቡባዊ ሴኔጋልን ለመገንጠል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ነበር
በሀገሪቱ መንግስት እና በታጣቂዎቹ መካከል የሰላም ስምምነት ተፈርሟል
የሴኔጋል መንግስት እና ደቡባዊ ሴኔጋልን ለመገንጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች እርቅ አወረዱ።
በሴዛር አቶቴ ባዲያቴ የሚመራው የካሳማንቼ ኃይሎች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (MDFC) ላለፉት 40 ገደማ ዓመታት ነፍጥ አንግቦ በደቡባዊ ሴኔጋል ሲንቀሳቀስ ነበር።
ሆኖም አሁን ትጥቅ አውርዶ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ መስማማቱን አስታውቋል።
ስምምነቱን በፀጋ የተቀበሉት ፕሬዝዳንት ማኪ ሳልም ከሴዛር አቶቴ ጋር ከትናንት በተስቲያ ሐሙስ ተፈራርመዋል እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ።
ማኪ ሳል የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ናቸው።
ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እንደሚያስችል ተስፋ የተጣለበት የሰላም ስምምነት በጊኒ ቢሳው ነው የተፈረመው።
ስምምነቱ በሸምጋዮች ጥረት እውን የሆነ ሲሆን፤ ማኪ ሳል አማጺ ቡድኑን ከመንግስታቸው ጋር ለማሸማገል ላደረጉት ጥረት የጊኒ ቢሳውን ፕሬዝዳንት ዑማሮ ሲሶኮ ኢምባሎን አመስግነዋል።
የካሳማንቼ ኃይሎች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (MDFC) ነፍጥ አንግበው ለረጅም ዓመታት ከተንቀሳቀሱ የአፍሪካ አማፂ ቡድኖች መካከል አንዱ ነው።