ባክሙት 16 ወራት ባስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ረጅም ጊዜ የፈጀ እና ደምአፋሳሽ ጦርነት የተካሄደባት ከተማ ነች
የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ዋግነር ግሩኘ አለቃ የቭገኒ ኘሪጎዚን ከባድ ጦርነት ሲካሄድባት የነበረችውን ባክሙትን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቋል።
ነገርግን ዩክሬን ጦርነቱ በምስራቅ ግንባር መቀጠሉን ገልጻለች።
ፕሪጎዚን ይህን ያስተላለፈው ወታደራዊ ልብስ በመልበስ የሩሲያን እና የዋግነርን አርማ በያዙ ተዋጊዎች ፊት ነው።
ሮይተርስ ፕሪጎዚን የታዩበት ቦታ ባክሙት መሆኑን ማረጋገጡን ገልጿል። ፕሬጎዚን ባስተላለፉት የቴሌግራም ቪዲዮ መልእክት "ባክሙትን ተቆጣጥረናል" ሲሉ ተናግረዋል።
ነገርግን የዩክሬን ጦር ቃል አቀባይ ሰርሂ ቸርቫቲ እንደተናገሩት "ይህ ሀሰት ነው፤ የኛ ኃይል እየተዋጋ ነው" በማለት የፕሪጎዚንን መግለጫ አስተባብለዋል።
ባክሙት 16 ወራት ባስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ረጅም ጊዜ የፈጀ እና ደምአፋሳሽ ጦርነት የተካሄደባት ከተማ ነች።
ፕሪጎዚን በፈረንጆቹ ከግንቦት 25 ጀምሮ ለእረፍት ከባክሙት እንደሚወጡ እና ቦታው በሩሲያ መደበኛ ጦር እንደሚተካም ገልጸዋል።
ፕሪጎዚን የሩሲያ ጦር አስፈላጊውን የተተኳሽ ድጋፍ ባለማቅረቡ የዋግነር ጦር መክፈል የማይገባውን ዋጋ ከፍሏል ሲል ተጋጋሚ ቅሬታ አሰምቷል።